1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ዳግም አገልግሎት መጀመሩ

ዓርብ፣ ጥር 14 2013

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ክልል በነበረው ውጊያ የደረሰውን የኩባንያውን የአገልግሎት መቋረጥ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ እንዳልቻለ ገለፀ። ኩባንያው በውቅሮ፣ ደገ ሐሙስ፣ አዲግራት እና ነጋሺ ከማክሰኞ አንስቶ በአንዳንድ ቦታዎች ዳግም አገልግሎት መጀመሩን በመጥቀስ የጥገና ሥራ ትናንት እየተሠራ እንደነበረም አክሏል

https://p.dw.com/p/3oJ0T
Äthiopien Firehiwot Tamiru
ምስል Solomon Muche/DW

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ክልል በነበረው ውጊያ የደረሰውን የኩባንያውን የአገልግሎት መቋረጥ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ እንዳልቻለ ገለፀ። ኩባንያው በውቅሮ፣ ደገ ሐሙስ፣ አዲግራት እና ነጋሺ ከማክሰኞ አንስቶ በአንዳንድ ቦታዎች ዳግም አገልግሎት መጀመሩን በመጥቀስ የጥገና ሥራ ትናንት እየተሠራ እንደነበረም አክሏል። በተጠቀሱት ቦታዎች ሰዎች በስልክ ደውለው ማነጋገር መቻላቸውን ዶይቸ ቬለ የደረሰው መረጃ ያመላክታል። ኩባንያው በግማሽ ዓመቱ ከ25 ቢሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉን ገልፆ በሕግ የተፈቀደ የካፒታል መጠኑን ወደ አራት መቶ ቢሊዮን ማሳደግ እንዲችልና በባንኮችና የፋይናንስ ተቃማት ሲሰጥ የተለመደውን የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ከመንግሥት ፍቃድ ማግኘቱንም ትናንት በሰጠው መግለጫ ዐሳውቋል። ለዝርዝሩ ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ