1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመጉ ቤንሻንጉል ውስጥ የዜጎች መብት እንዲከበር አሳሰበ 

ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2013

መንግሥት የዜጎችን የመዘዋወር ነጻነት እና መብት እንዲያስከብር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። ጉባኤው ለዶይቸ ቬለ (DW) ዛሬ በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈጸሙ አሳዛኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ መታረም አለባቸው ብሏል።

https://p.dw.com/p/3jAmA
Karte Äthiopien Metekel EN

«አሳዛኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ መታረም አለባቸው»

መንግሥት የዜጎችን የመዘዋወር ነጻነት እና መብት እንዲያስከብር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። ጉባኤው ለዶይቸ ቬለ (DW) ዛሬ በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የተፈጸሙ አሳዛኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ መታረም አለባቸው ብሏል። ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡም ጉባኤው ጠይቋል። ጉባኤው፦ «መንግሥት በቤንሻንጉል ክልል የሰዎችን በሕይወት የመኖና የአካል ደኅንነት መብት ይጠብቅ» ሲልም መስከረም 18 ቀን፣ 2013 ዓ.ም ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫው አሳስቧል። 

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶትስ ስለሺ
ኂሩት መለሰ