1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አፍሪቃ፣የፀጥታው ምክር ቤት አባልነት ጥያቄ 

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2014

በሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ኘሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት የአፍሪቃ ሃገሮች ያነሱትን ዐሳብና ጥያቄ መግፋትና ከሌሎች የሥስተኛው የዐለም ሃገራትና በምዕራቡ ዓለም አመለካከቱን ከሚያራምዱ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጭምር አጋር ማሰባሰብ አለባቸው

https://p.dw.com/p/450Uu
USA | UN Sicherheitsrat in New York zur Lage in Äthiopien
ምስል Manuel Elias/Xinhua/picture alliance

በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የአፍሪቃ ዉክልና

አፍሪቃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ  አባል እንድትሆን የአፍሪቃ ሃገራት  ያቀረቡትን ጥሪ ገፍተው መቀጠል እንደሚኖርባቸው ተገለጸ። በሞርጋን ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ኘሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ለዶይቸ ቨለ እንደገለጹት የአፍሪቃ ሃገሮች ያነሱትን ዐሳብና ጥያቄ መግፋትና ከሌሎች የሥስተኛው የዐለም ሃገራትና በምዕራቡ ዓለም አመለካከቱን ከሚያራምዱ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጭምር አጋር ማሰባሰብ አለባቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፍጥነት የሚለዋወጠውን የዓለም ሁኔታ መቋቋም አለበት ያሉት ኘሮፌሰር ጌታቸው አሁን ያለው ዓለም አቀፍ ሁኔታ ድርጅቱ ሲቋቋም ከነበረው ፈፅሞ የተለየ ነው ብለዋል። 
ታሪኩ ኃይሉ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ