1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አድማጮች ፤ አዲሱን ዓመት በተስፋ ጀምረናል

ሐሙስ፣ መስከረም 7 2013

ኢትዮጵያዉያን በአዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን ሰንቀዉ፤ ዓመቱ የጤና እና የሰላም ይሁንልን ብለዉ አዲሱን ዓመት ተቀብለዋል። 2012 ዓመትስ እንኳን ሄደልን ፤በሽታዉ  ኮሮናዉ፤ ግጭቱ ፤ግድያዉ፤ተቃዉሞዉ፤ ጎርፉ፤ አንበጣዉ ፤ በሰላም ሸኝተን፤ አዲሱን ዓመት በሰላም ተቀብለናል ይላሉ የዝግጅታችን ተሳታፊዎች። እንኳን አደረሳችሁ!

https://p.dw.com/p/3iddp
ÄthiopienTraditioneller Kaffee in Addis Abeba
ምስል picture alliance/dpa/Photoshot

«የአዲስ ዓመት አቀባበልና መልካም ምኞት»

 

ኢትዮጵያዉያን በአዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን ሰንቀዉ፤ ዓመቱ የጤና እና የሰላም ይሁንልን ብለዉ አዲሱን ዓመት ተቀብለዋል። 2012 ዓመትስ እንኳን ሄደልን ፤በሽታዉ ኮሮናዉ፤ ግጭቱ ፤ግድያዉ፤ተቃዉሞዉ፤ ጎርፉ፤ አንበጣዉ ፤ በሰላም ሸኝተን፤ አዲሱን ዓመት በሰላም ተቀብለናል ይላሉ የዝግጅታችን ተሳታፊዎች።  እንኳን አደረሳችሁ!   ኢትዮጵያዉያን ሁሉ እንደየአቅማቸዉ ዓመት በዓልን ደመቅ አድርገዉ ተቀብለዋል። ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም እንዲሁ እንደየአቅማቸዉ እና እንደሚችሉት ከአገር ቤት ይዘዉ የመጡትን የባህል አልባሳት አድርገዉ ዶሮ ሰርተዋል፤ ባይሆን ባይሆን ቡና አፍልተዉ ተቃምሰዋል። አብዛኞች ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት ከሆነ ዘንድሮ አሮጌዉ ዓመት መቼ አልፈህ አሮጌዉ ተብለህ፤ ተብሎ በጉጉት ተጠብቆ በመቆየቱ አዲሱን ዓመት የተቀበልነዉ በልዩ ሁኔታ ነዉ ይላሉ።  አዲሱ 2013 ዓመት ለኢትዮጵያዉያን ሁሉ የጤና የሰላም የመተሳሰብ እና የብልጽግና ዓመት እንዲሆን እንመኛለን። የባህል መድረክ ተሳታፊዎች አዲሱን ዓመት እንዴት ተቀበላችሁ አሮጌዉንስ እንዴት ሸኛችሁ ስንል ጠያይቀን ቅንብር ይዘናል። ሙሉ ቅንብሩን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ