1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲስ ወረርሽን በድሬደዋ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 7 2011

ምሥራቅ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው በሽታ ብዙዎችን ማዳረሱ እየተነገረ ነው። በተለይ የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ከዓመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ኅብረተሰቡን ካጋጠመው የደንጊ በሽታ ምልክቶች ጋር ይቀራረባል የተባለው ይህ ህመም ስሜቱ ግን ወትሮ ካወቁት ይለያል ይላሉ።

https://p.dw.com/p/3NqYf
Äthipopien Leiter des Dire Dawa Health Bureu Dr. Fuad Kedir
ምስል DW/Mesay Teklu

«አዲሱ በሽታ «ቺኩን ጉንያ» ነው ተብሏል»

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የጤና ቢሮ ኃላፊ እስካሁን በአዲሱ በሽታ ከ3 ሺህ ሰዎች በላይ በመያዛቸው በከተማው ወረርሽኝ መከሰቱን ይፋ አድርገዋል። «ቺኩንጉንያ» የተባለው አዲሱ በሽታ በአስተዳደሩ አጎራባች ክልሎችም ተከስቶ እንደነበርም ተናግረዋል። 

በ2006 ዓ.ም ለመጀመርያ የተከሰተው የደንጊ በሽታ ምልክቶችንም ሆነ የመከላከያ ዘዴዎችን በተሻለ ተገንዝቧል የሚባለው የድሬደዋ ህብረተሰብም ሆነ በአካባቢው ያሉ ህክምና ተቋማት የቻሉትን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ደንጊ በሚል ከሚያውቁት ወረርሽኝ ህመም ጋር በሚቀራረብ ሰሞኑን ብዙዎች የታመሙበት በሽታ ስሜት ግን ይለያል ይላሉ በርካቶች። በእርግጥም ብዙዎችን አቅም አሳጥቶ አልጋ ላይ ጥሏል፤ ታመው ወደ ግል እና የመንግሥት ህክምና ተቋማት እንዲሄዱም አስገድዷል። በዚሁ ሰሞን በዚሁ ሳቢያ ታመው ቤት ውለው የነበሩ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ተከታዩን ብለዋል። የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፎሃድ ከድር ከድር ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአስተዳደሩ "ቺኩንጉንያ" የተባለ አዲስ የበሽታ ወረርሽኝ መከሰቱን አስታውቀዋል። በአካባቢው ቀደም ሲል ይታወቁ ከነበሩት ወባ እና ደንጊ በሽታዎች የህመም ምልክት ጋር የሚቀራረብ ስሜት ያለው ይኸው በሽታ  ቀደም ሲል በአስተዳደሩ አጎራባች ክልል አካባቢዎች ተከስቶ እንደነበር የጠቀሱት ዶ/ር ፎሀድ  ምናልባትም መነሻው ከዚያ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። የምርመራ ውጤት ይለያይ እንጂ ብዙ ቁጥር ያለው ኅብረተሰብ የደንጊ ህመምና ተቀራራቢ ስሜት ባለው የአሁኑ «ቺኩንጉንያ» የተባለው ወረርሽ በሽታ ስሜቶች መያዛቸውን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄ ዶ/ር ፎሃድ ተከታዩን ማብራርያ ሰተዋል። የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን የተናገሩት የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፎሀድ ግንዛቤን ከመፍጠር ጀምሮ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአስተዳደሩ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። በጣት ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ወባ ትልቅ ፈተና የነበረባት ድሬደዋ ወባን ለመከላከል የተደረገው ጥረት ውጤት ማምጣት ሲጀምር ደንጊ አሁን ደግሞ አዲስ የተባለው «ቺኩንጉንያ» በወረርሽኝ መልክ የተከሰት ፈተና ሆኗል። የተቋሙ ባለሞያዎች በሽታው ገዳይ አይሁን እንጂ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አስገንዝበዋል። መሳይ ተክሉከድሬደዋ መሳይ ተክሉ ዘገባ አለው።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ