1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የኤርትራ ሶማሊያ ግንኙነት

ሰኞ፣ ሐምሌ 23 2010

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ዛሬ ሰኞ ጧት “የኤርትራ እና ሱማሊያ ወንድማማች ግንኙነት እና ሁሉን ዐቀፍ ትብብር” የተሰኘ ባለ አራት ነጥብ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/32L3h
Bildkombo l Somalischer Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed und Eritreische Präsident Isaias Afwerki


ሁለቱ ሀገሮች ለ15 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውንም እንደገና እንደሚጀምሩ እና በቅርቡም ኢምባሲዎቻቸውን በሞቃዲሾ እና አሥመራ እንደሚከፍቱ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ድረ ገጹ ላይ ይፋ ባደረገው የስምምነቱ ሰነድ ላይ ተገልጧል፡፡ ከዚህም ሌላ ሶማሊያ የተመድ በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳም ጠይቃለች።  

ቻላቸው ታደሰ
አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ