1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዲሱ የምርጫ ሕግ ተቃዉሞ ገጠመዉ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 28 2011

ገዢዉን ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ 107 የፖለቲካ ማሕበራትን የሚያስተናብረዉ ምክር ቤት ዛሬ እንዳስታወቀዉ የምርጫ ሥነ-ምግባርና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ የተባለዉ ደንብ የፀደቀዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሳይሰጥ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3Ox9e
Äthiopien | Presseerklärung zu Neuwahlen, Vorsitzender Mussa Adene
ምስል DW/S. Muche

አዲሱ የምርጫ ሕግ እንዳወዛገበ ነዉ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የሐገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያፀደቀዉን የምርጫ ደንብ ዉድቅ አደረገዉ።ገዢዉን ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ 107 የፖለቲካ ማሕበራትን የሚያስተናብረዉ ምክር ቤት ዛሬ እንዳስታወቀዉ የምርጫ ሥነ-ምግባርና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ የተባለዉ ደንብ የፀደቀዉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሳይሰጥ ነዉ።የጋራ ምክር ቤቱ አክሎ እንዳለዉ በመጪዉ ዓመት ሊደረግ የታቀደዉ ምርጫ አዲስ በፀደቀዉ ደንብ ከሚመራ ይልቅ የምርጫዉ ጊዜ መገፋቱን ይደግፋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ