1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አከራካሪው አዲሱ የኮንጎ ማዕድን የማውጣት ሕግ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 29 2010

የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ፕሬዚደንት ሰሞኑን የፈረሙት አዲሱ የማዕድን የማውጣት ሕግ ከትልቆቹ ተቋማት ተቃውሞ ገጠመው። በአዲሱ ሕግ መሰረት፣ ኮባልት እና ወርቅን ከመሳሰሉ ማዕድናት የሚገኘው ግብር በጉልህ ከፍ ብሏል። ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ የኮንጎ ሕዝብ ከዚህ አዲስ ግብር ተጠቃሚ መሆን መቻሉ እያጠያየቀ ነው።

https://p.dw.com/p/2vd9G
Konfliktfreie Kalimbi-Mine Kongo
ምስል DW/J. van Loon

የኮንጎ ማዕድን

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ትልቆቹ ተቋማት አዲሱ የማዕድን ሕግ ለኢንዱስትሪው እና ለአህጉሩ ባጠቃላይ ጎጂ ሊሆን ይችላል በሚል የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ጆሴፍ ካቢላ ሕጉን እንዳይፈርሙ ያደረጉት ጥረታቸው ሳይሳካ ቀርቷል።


የኮንጎ መንግሥት ባወጣው አዲስ ሕግ መሰረት፣ የማዕድን ተቋማት ወደፊት ለመንግሥቱ ተጨማሪ ግብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።   "ተቋማቱ ለጥሬ አላባ በአሁኑ ጊዜ የሚከፍሉት ወደ ሁለት ከመቶ የሚጠጋው ግብር ወደ ሶስት ተኩል ከመቶ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል። ጥሬ አላባው ስልታዊ ነው ተብሎ ከታሰበም ለምሳሌ እንደ ኮባልትን የመሰለ እስከ 10% ሊደርስ እንደሚችል ነው የተጠቆመው። ከዚህ በተጨማሪ ዋጋቸው የጨመሩ ጥሬ አላባዎች  ላይ እስከ 50 % ልዩ ግብር እንዳይታዘዝ አስግቷል።

Joseph Kabila Präsident der Demokratischen Republik Kongo
ምስል picture-alliance/dpa/M. Kappeler

 
የማዕድኑ ህግ ተግባራዊ ሲሆን እያንዳንዱ ተቋም የሚያቀርበውን ስጋት እንጠብቃለን። ስጋታቸውንም በየሚንስቴሩ ካሉ ጠበብት፣ ከመንግሥት እና ከራሳቸው ከተቋማቱ ጋር በጥሞና እንመለከታለን። እያንዳንዱን ቅሬታ ከተመለከትን እና ከሚመለከታቸው ኮሚቴዎች ጋር ከመከርን፣ እንዲሁም፣ በማዕድኑ መመሪያ ላይ አስፈላጊውን ለውጥ ካደረግን በኋላ ዘገባ እናወጣለን።  በኛ ግምት፣ መፍትሔው ያለው በማዕድኑ መመሪያ ላይ ነው።    

ኮንጎ በተፈጥሮ ሀብት በዓለም ሶስተኛ ናት። የዓለም አንድ ሶስተኛው ኮልታን ፣ ግማሹ ያህል ኮልታን ለዘመናዮቹ የእጅ ስልኮች እና የኤሌክትሪክ መኪኖች የሚያስፈልገው ኮባልት የሚገነው ኮንጎ ውስጥ ነው።  ባለፉት ሁለት ዓመት ብቻ የአንድ ቶን ኮባልት ዋጋ ከ18,500 ወደ 63,000 ዩሮ ከፍ ብሏል። ኮንጎ የግዙፍ የነሀስ ፣ ወርቅ፣ አልማዝ እና ሌሎች የከበሩ ድንጋዮች ንጣፍም ባለቤት ናት።
ይህ ለብዙ ተቋማት ጥሩ ንግድ ገቢ ምንጭ ,ው፣ ወደ 83 ሚልዮኑ የኮንጎ ሕዝብ ግን ተጠቃሚ አይደለም። ከዓለም ድሆች ሀገራት አንዷ  በሆነችው ኮንጎ ውስጥ ይኸው ገቢ በጥቂት ባለስልጣናትና ዓለም አቀፍ ባለተቋማት እጅ ውስጥ ነው የሚቀረው። በፓራዳይዝ ሰነዶች መሰረት፣ የስዊትዘርላንዱ ግሌንኮር ተማዕድን ተቋም በአጠያያቂ ውል አማካኝነት ማዕድን የማውጣት ፈቃድ አግኝቷል። የሲቭል ማህበረሰቦች ቀደም ካለ ጊዜ ጀምረው በጥሬ አላባ ማውጣቱ ዘርፍ ላይ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀዋል። 
የእስካሁኑ ሕግ በ2002 የወጣ ነው። ሕዝቡ አሁን በተፈረመው አዲስ ሕግ ጥቅም በሚያስገነው የግብር ጭማሪ ጥቅም ሊያገን ይችል ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ይሁንና፣ ይህን እንደሚጠራጠሩት የማዕከላይ አፍሪቃ ኤኩሜኒካል መረብ የተባለው መያድ ባልደረባ ጌዚነ አመስ ገልጸዋል።
« አዲሱ ህግ ባጠቃላይ በኮንጎ ሕዝብ ዘንድ ድጋፍ አግንቷል። ይሁንና፣ ልክ ካሁን ቀደም በሀገሪቱ እንደወጡ ሌሎች ሕጎች ነው የሚታየው። በወንጀለኛ መቅጫው ዘርፍ ም ጥሩ ሕጎች አሉ። ግን፣ ሕጎችን ተግባራዊ የሚሆኑበት አሰራር አሁንም ተጓድሎ ይገኛል። »
ምክንያቱም በዓለም ኮንጎ ሙስና የተስፋፋባት ሀገር ናተ። በትራንስፓረንሲ መዘርዝር ውስጥ ከ180 ሀገራት 161 ደረጃ ላይ ናት።  የጥሬ አላባ ማውጣቱ ዘርፍ በግልጽነት በሌለው የማፊያ ዓይነት አሰራር መዋቅር የተተበተበ እንደሆነ ጌዚኔ አመስ አስረድተዋል። 
"እንደ ጠበብት ግምት፣  በ2016 ስልጣና መልቀቅ የነበረባቸው ግን ስልጣኑን የሙጥኝ ያሉት ፕሬዚደንት ካቢላ እና ቤተሰባቸው ስም ከሙስናው ጋር በተያያዘ አዘውትሮ ስለሚነሳ፣ አዲሱ ሕግ ብዙም የሚቀይረው ነገር አይኖርም ። 

Neues Bergbaugesetz in der RD Kongo
ምስል Getty Images/AFP/S. Tounsi

አርያም ተክሌ/ዳንየል ፔልስ

ልደት አበበ