1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንድ መንደር በሁለት አገር ሞደለሮይትዝ

ሰኞ፣ ኅዳር 1 2012

ጀርመን ከሰሞኑ ምዕራብ እና ምሥራቅ በሚልክ ከፍሏት ለዓመታት የቆየው ግንብ የፈረሰበትን 30ኛ ዓመት ትዘክራለች። ከውህደቱ በኋላ ያለውን ገፅታ ለመቃኘት ዶይቼ ቬለ ከተለያዩ የአፍሪቃ ቋንቋ ስርጭት ክፍሎች የተውጣጡ ጋዜጠኞችን ግንቡ ተዘርግቶ ወደነበረበት አካባቢ ልኳል።

https://p.dw.com/p/3QyOU
Deutschland Mödlareuth Tower
ምስል DW/E. Bekele

«የበርሊን ግንብ ከፈረሰ 30 ዓመት ይደፍናል»

 በዚህ የጋዜጠኞች ቡድን ውስጥ ባልደረባችን እሸቴ በቀለ ይገኛል። ለዛሬ 1400 ኪሎ ሜትር የሚያካልለው ግንብ ቅሪት ያለባት ከተማ ሞደለሮይትዝን  ያስቃኘናል።  በቱይሪንገን እና በባየርን ግዛቶች አዋሳኝ ድንበር ላይ የምትገኘው የሞደለሮይትዝ መንደር የጀርመን መከፋፈል እና ውኅደት ምልክት ተደርጋ ትወሰዳለች። ግንቡ ከፈረሰም በኋላ የቀድሞዎቹ ምሥራቅ እና ምዕራብ ጀርመን ክፍፍል ልዩነት አሻራ በመንደሯ ይታያል። እሸቴ በቀለ ተጨማሪ ዘገባ አለው። 

እሸቴ በቀለ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ