1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት  

ሰኞ፣ ጥቅምት 2 2013

የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና ፣ ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለDW በስልክ እንደተናገሩት በሃያ ስድስት ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው አንበጣ በአስራ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። መንግስት ችግሩን ለመከላከል

https://p.dw.com/p/3jp1T
Äthiopien Heuschreckenschwarm
ምስል Mesay Teklu/DW

አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት  

አንበጣ በድሬዳዋ የገጠር ቀበሌዎች ያደረሰው ጉዳት  

ከቀናት በፊት በድሬደዋ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሃያ ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በአርሶ እና አርብቶ አደሩ ኅብረተሰብ የደረሱ ሰብሎች ላይ መጠነኛ እና ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡ መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመደገፍ እና ችግሩን ለመከላከል እየሠራሁ ነው ብሏል፡፡ 
በድሬደዋ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች መካከል በሁሉል ሞጆ እና ዋሂል ገጠር ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ለDW እንደገለፁት በአካባቢያቸው የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የድሬደዋ አስተዳደር ግብርና ፣ ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ለDW በስልክ እንደተናገሩት በሃያ ስድስት ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው አንበጣ በአስራ ሰባቱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው መንግሥት ችግሩን ለመከላከል ምን እየሰራ እንደሆነ አስረድተዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎቹ አርሶ አደሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ መሀመድ ዑስማን በሰጡት አስተያየት መንግሥት ቀድሞ የመከላከል ሠራ ሊሠራ ይገባ እንደነበር ጠቅሰው አሁንም ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአካባቢዎቹ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመስክ ምልከታ ማደረጋቸውን  ተከትሎ ምክትል ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ በአርሶና አርብቶ አደሩ ዘንድ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ በመግለፅ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ትናንት በተዘዋወርኩባቸው የዋሂል ክላስተር ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደረሱ ሰብሎች ላይ ደረሰው ጉዳት ወትሮውኑ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ምርት በማምረት አብዛኛውን ግዜ በምግብ እህል ድጋፍ ላይ ባተኮረው የሴፍትኔት መርሀ ግብር ይደገፍ ለነበረው አርሶ እና አርብቶ አደር መጪው ጊዜ ከባድ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

Äthiopien Heuschreckenschwarm
ምስል Mesay Teklu/DW

መሳይ ተክሉ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 


--