1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጡረተኞቹ ስደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል” በሚል ተፈርዶባቸዋል

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 13 2010

በፈረንሳይ የኤክስ ኦ ፕሮቮንስ ግዛት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለስደተኞች እርዳታ በሰጡ በአራት ፈረንሳውያን ጡረተኞች ላይ ባለፈው ሳምንት ያስተላለፈው ብይን መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ፍርድ ቤቱ ደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል፣ ሕግም ተላልፋችኋል” በሚል በጡረተኞቹ ላይ የእገዳ እና የገንዘብ ቅጣት ብያኔ አስተላልፏል፡፡

https://p.dw.com/p/2prJn
Frankreich Abschiebung von Asylsuchenden
ምስል picture-alliance/NurPhoto/J. Mattia

ጡረተኞቹ ስደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል” በሚል ተፈርዶባቸዋል

የፈረንሳይ ፍርድ ቤት በጡረተኞቹ ላይ ብይን ያስተላለፈው ባለፈው ዓመት በፈረንሳይ እና ጣሊያን ድንበር አካባቢ ሕጻናትን ጨምሮ ስድስት ስደተኞችን “በመኪናችሁ አጓጉዛችኋል፣ ሕግም ተላልፋችኋል” በሚል ነበር፡፡ የተከሳሾቹ የይግባኝ ውሳኔ ከተሰማ በኋላም ፈረንሳይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፍም ወጥተዋል፡፡ ይህ መሰሉ ንቅናቄ በፈረንሳይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየታየ ባለው የስደተኞች አቀባበል ችግር ላይ መሻሻል እንዲኖር ግፊት እንደሚፈጥር እየተነገረ ነው፡፡ የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተከሳሾቹን ጡረተኞች አነጋግራ ያጠናቀረችውን ሙሉ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡   

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ