1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የትራምፕ አስተያየትና የአውሮጳ ሕብረት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 17 2013

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ዓርብ በህዳሴው ግድብ እና የኢትዮጵያ አቋም ላይ የሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣና ለተቃውሞ ያስነሳ ብቻ አልነበረም። ጉዳዩን እስካሁንም የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳበ ዐቢይ ጉዳይ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/3kVVR
Äthiopien Addis Abeba | Report | Grand Ethiopian Renaissance Dam
ምስል DW/N. Desalegen

«የአውሮጳ ሕብረት አስተያየት»

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ዓርብ በህዳሴው ግድብ እና የኢትዮጵያ አቋም ላይ የሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣና ለተቃውሞ ያስነሳ ብቻ አልነበረም። ጉዳዩን እስካሁንም የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ትኩረት የሳበ ዐቢይ ጉዳይ ሆኗል። ትራምፕ ሱዳን ከእስራኤል ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት የተስማማች መሆኗን ለመግለጽ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለህዳሴው ግድብ አንስተው ኢትዮጵያ በቀረበላት ማግባቢያ ሃሳብ ባለመስማማቷ ግብፅ ግድቡን በቦምብ ብታፈርሰው አትጠየቅም አይነት አስተያየት መስጠታቸው በኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ ነው ያስከተለው። የአውሮጳ ሕብረት ግድቡን አስመልክቶ በአፍሪቃ ሕብረት አማካኝነት የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ሲያሳስብ፤ በቤልጂየም የህዳሴው ግድብ አስተባባሪ ግብረኃይል በበኩሉ አጋጣሚው የብዙዎችን ቀልብ መሳቡን በአዎንታዊ ጎኑ እንደሚወስደው አመልክቷል። 

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ