1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪዉ የአዲስ አበባ ከንቲማ ሹመት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 17 2010

ኢንጂነር ታከለ ኡማ መሾማቸዉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ መወያያ ርቅስ እንደሆኑ ነዉ። የመዲና አዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ መሆናቸዉን የሚቃወሙ በከተማዋ ተወልደዉ ስላላደጉ ከተማዋን በቅጡ ለማስተዳደር ጉድለት አለባቸው፣ ብሔር ዘመም አቋማም ስላላቸዉም፤ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች መኖርያ አዲስ አበባን ያለ አድሎ ማስተዳደራቸዉ አጠራጣሪ ነዉ ይላሉ።

https://p.dw.com/p/321d4
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሾምዋቸዉ ስለተማመኑባቸዉ ነዉ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነዉ መሾማቸዉ ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል።አንዳንዶች መንግሥት አቅም አለዉ ብሎ እስካመነበትና እስከሾመ ድረስ መቀበል አለብን ሲሉ ሌሎች ደግሞ በከተማዋ ነዋሪ የሆነ የከተማዋን ችግር በቅርበት የሚዉቅ ግለሰብ በምክር ቤቱ ዉስጥ ጠፍቶ ነዉ ወይ መንግስት ሌላ አማራጭን የፈለገዉ ሲሉ ይጠይቃሉ? በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በዶይቼ ቬለ የፌስ ቡክ ገፅ አድማጮቻችንን እና ተከታታዮቻችን አወያይተናል።  

ኢንጂነር ታከለ ኡማ መሾማቸዉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ መወያያ ርቅስ እንደሆኑ ነዉ። የመዲና አዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ መሆናቸዉን የሚቃወሙ በከተማዋ ተወልደዉ ስላላደጉ ከተማዋን በቅጡ ለማስተዳደር ጉድለት አለባቸው፣ ብሔር ዘመም አቋማም ስላላቸዉም፤ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች መኖርያ አዲስ አበባን ያለ አድሎ ማስተዳደራቸዉ አጠራጣሪ ነዉ ይላሉ። ሌሎች በበኩላቸዉ መንግስት በብቃቱ ተማምኖ እስኮሾማቸዉ ድረስ ብሔራቸዉም ሆነ ከየት ይምጡ ማጣራቱ በዚህ ክፍለ ዘመን መነሳት የሌለበት ጥያቄ ነዉ ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ እስከዛሬ መተንፈስ እንኳ ሳንችል ቀርተን የተሻለ መንግሥት ሲመጣ እንዲሰራ ትንሽ ጊዜ መስጠት አለብን ሲሉም ይናገራሉ። 
ከአዲስ አበባ ብዙም ሳይርቁ እንደኖሩ መናገራቸዉ የተገለፀዉ እና ከዚህ ቀደም በተለያዩ የኦሮምያ ክልልሎች በከንቲባነት ያገለገሉት አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሁሉ ኢትዮጵያዉያን መኖርያ መሆንዋን መናገራቸዉ ተዘግቦአል።  
በጋሻዉ ቢተዉ ከተባሉ አድማጫችን የደረሰን የፅሑፍ መልክት ደሞ እንዲህ ይላል። 
« ኢንጂነር ታከለ ኡማን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አድርገው የሾሙት ዶር. አብይ አህመድ የሀገሪቱን የፖለቲካ እሽክርክሪት ከህወሀት የበላይነት ወደ ኦህዴድ የበላይነት አሸጋግረውታል እየተባሉ ሲተቹ ሰንብተዋል። በብሄርተኝነት አቋማቸው እና የአ.አ ማስተር ፕላን ከፊንፊኔ ዙሪያ ከተሞች ጋር በተያያዘ ያራምዱት በነበረ አቋም ለዚህ ስልጣን ብቁ አይደሉም የሚሉ አስተሳሰቦች በስፋት እየተራገቡ ይገኛሉ። የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሙስና በተገኘ ሀብት ፋብሪካ ለመትከል ወይንም ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎችን ለመገንባት ተብሎ ድሀ የኦሮሚያ አርሶ አደሮች ሲፈናቀሉ ማየት አልፈልግም ብለው በፊታውራሪነት ለድሀው ህዝብ በመከራከራቸው ይሄው ዛሬ ለአዲስ አበባ እድገት ፀር ናቸው የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው እየተወቀሱ ይገኛሉ።
ሌላው ዶር. አብይ እየታገሉ ያሉት ውሉ በተተበተበ የሙስናና የዘረኝነት ሰንሰለት ውስጥ ካሉ ክንዳቸው በገንዘብና በኔትወርክ በፈረጠመና መምጫቸው ከማይታወቅ የቀን ጅቦች ጋር በመሆኑ በእውቀቱ በጥንካሬው እና በለውጡ ሂደት ውስጥ ባለው አቋም የሚያውቀውን ሊያግዘው የሚችለውን ሰው ከአጠገቡ እንዲሆን ማድረጉ ጥቅም እንጅ ጉዳት የለውም። እናም እያንዳንዳችን ለለውጡ መሳካት መታገልን እንቀጥል»o የሚል ሰፊ አስተያየት አስፍረዋል።

የአድማጮች አስተያየት የተካተተበትን ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

 

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ