1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አቶ ስበሐት ነጋና የህወሓት አመራር በቊጥጥር ስር ዋሉ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 30 2013

የሕወሓት የረጅም ጊዜ ሊቀመንበርና አንጋፋ አባል አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት «የጥፋት ቡድን አመራሮች» ያላቸውን ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ገለፀ።

https://p.dw.com/p/3nhq6
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የሕወሓት የረጅም ጊዜ ሊቀመንበርና አንጋፋ አባል አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት «የጥፋት ቡድን አመራሮች» ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ገለፀ። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መከላከያ ሚንስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበዉ አቶ ስብሐትን፣ ላለፉት 27 ዓመታት «የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ፣ ያስተባበረ እና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሠራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሠራዊቱን ያስጨፈጨፉ» ብሏቸዋል።የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ይኽንኑ ለኢዜአ መግለጣቸውም ተዘግቧል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ትናንት 4 የሕወሓት ባለስልጣናት መገደላቸዉንና ዘጠኝ መማረካቸዉን ዐስታዉቆ ነበር። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ