1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አብን የዐማራ ክልል መግለጫን ነቀፈ 

ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2011

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በምኅጻሩ አብን፦ «የትኛውም ክልል አዲስ አበባ ላይ የተለየ ጥቅም ሊጠይቅ አይገባውም» አለ።  የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር በቅርቡ አምቦ ላይ ባደረጉት ንግግር ሥለ አዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄን የጠቀሱትን፣ ንቅናቄዉ «የዐማራን ህዝብ እና የሌሎችን ኢትዮጵያውያኖች መብት እና ጥቅምን ይጋፋል» ብሏል።

https://p.dw.com/p/3HSOm
Äthiopien Addis Abeba - Nama Hauptquartier
ምስል DW/ S. Mantegaftot Sileshi

«የዐማራን ህዝብ እና የሌሎችን ኢትዮጵያውያኖች መብት እና ጥቅምን ይጋፋል»

የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በምኅጻሩ አብን፦ «የትኛውም ክልል አዲስ አበባ ላይ የተለየ ጥቅም ሊጠይቅ አይገባውም» አለ።  የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር በቅርቡ አምቦ ላይ ባደረጉት ንግግር ሥለ አዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄን የጠቀሱትን፣ ንቅናቄዉ «የዐማራን ህዝብ እና የሌሎችን ኢትዮጵያውያኖች መብት እና ጥቅምን ይጋፋል» ብሏል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበኩሉ፦ አዲስ አበባ ባለቤቶቿ ሁሉም ነዋሪዎቿ መኾናቸውን ዐስታውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር ሰሞኑን በአምቦ በአማራና ኦሮሞ የጋራ መድረክ ላይ አዲስ አበባን አስመልክተው የሰጡት መግለጫ ብዥታ መፍጠሩን የክልሉ መንግስት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

መግለጫው አያይዞም አዲስ አበባ ስታድግ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ሲፈናቀሉ መብታቸው እንዲጠበቅ በሚደረገው ትግል ማገዝ የግድ ኦሮሞ መሆን አይጠይቅም ብሏል፡፡ጥያቄው ፍትሐዊ እስከሆነ ድረስ ከኦሮሞ አርሶ አደር ጎን ተሰልፎ መታገል ወንድማማችነትን ያጎለብታል፣ ሰብዓዊነትም ነው ብሏል የአማራ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ፡፡

አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በህግ አግባብ ለመምራት በሚደረገው ጥረት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጎን ተሰልፎየመታገል ጉዳይ ከመርህ ውጭ በሆነ አግባብ መንቀፍ ግን የገመድ ጉተታ አዙሪትውስት ከመግባት ውጭ ሌላ ትርፍ የሌለው ጉዳይ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ልዩ ጥቅም የሚለው በህገመንግስቱ ያልተዘረዘረ በመሆኑ የቅሬታ ምንጭ እንደሆነ መለከተው መግለጫው በዚህም ምክንያት ሁላችንም በየአቅጣጫው የምንጓተትበት ጉዳይ ሆኗል ሲል አመልክቷል፡፡ መግለጫው እንደሚሳው ህገመንግስቱ እስኪሻሻል ሁላችንም የምንመራበት ሰነድ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተርና ምክትላቸው በጉዳዩ ላ አስተያየት እንዲሰጡ ቢጠየቁም ሁለቱም ፈቃደኛ እንደልሆኑ መልክተዋል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ-አብን የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መልካሙ ሹምዬ ለዶቼ ቬሌ (DW) እንደገለፁት አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንጂ ለተወሰነ ቡድን ኤደለችም ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርአዲስ አበባን አስመልክተው አምቦ ላይ ደረጉት ንግግርም አማራን ዝቅ ሚያደርግ ነው ብለዋል።

ዓለምነው መኮንን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ