1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አበበች ጎበና ሲታወሱ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 1 2013

በኢትዮጵያ በምግባረ ሠናይ ተግባር ተሰማርቶ የሚገኘዉ ሰዎች ለሰዎች ወይም በጀርመንኛዉ Menschen für Menschen የተሰኘዉ ድርጅት መሥራችና የበላይ ጠባቂ የነበሩት ካርል ሃይንዝ በም እንዲሁም  የቀድሞዉ የጀርመን ፕሬዚዳንት የዩአሂም ጋዉክ ባለቤት የክቡር ዶክተር አበበች ጎበናን የሕጻናት ማሳደግያ ድርጅትን ከጎበኙ መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/3wEl0
 Äthiopien, Addis Abeba | Daniela Schadt besucht Kinderschutzprojekt Agoheld
ምስል DW

የክብር ዶክተር አበበች ጎበና ሲታወሱ

በኢትዮጵያ በምግባረ ሠናይ ተግባር ተሰማርቶ የሚገኘዉ ሰዎች ለሰዎች ወይም በጀርመንኛዉ Menschen für Menschen የተሰኘዉ ድርጅት መሥራችና የበላይ ጠባቂ የነበሩት ካርል ሃይንዝ በም እንዲሁም  የቀድሞዉ የጀርመን ፕሬዚዳንት የዩአሂም ጋዉክ ባለቤት የክቡር ዶክተር አበበች ጎበናን  የሕጻናት ማሳደግያ ድርጅትን ከጎበኙ መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ።  

Äthiopien | Beisetzung Abebech Gobena
ምስል Seyoum Getu/DW

አበበች ጎበና ለበጎነት የማይሰለች እጅ ለሰብዓዊነት የማይታክት መንፈስ ይልዋቸዋል። 

አንጋፋዋ የበጎ ተግባር አገልግሎት ሰጪ፤ ሕጻናትን ከመንገድ አንስተው እና በተለያዩ መንገዶች ተቀብለው በማሳደግና በመንከባከብ የሚታወቁት አበበች ጎበና በ85 ዕድሜያቸው ባለፈው እሁድ ጠዋት 11፡00 ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ በኮሮና ተዋሲ ተይዘው ለ32 ቀናት ያህል በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና ተከታትለው በመጨረሻም ያረፉት እኚ የበጎ ፈቃደኝነት ተምሳለት ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በታላቅ ብሔራዊ ክብር ስርዓተ ቀብራቸውም ተፈፅሟል፡፡

የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በትንሹ ማዕከላቸውን ከመሰረቱ ወዲህ ከ1.5 ሚሊየን የላቁ ኢትዮጵያውያን በበጎነት እጃቸው ተዳሰዋል።  

 Äthiopien | Abebech Gobena und Karheinz Böhm in 2010
ምስል DW

ባሁን ወቅትም በዚሁ እሳቸው ለበጎ ተግባር መስርተው ባሳደጉት ማዕከል 7000 ሕጻናት በአጠቃላይም ከ350 የማያንሱ ዜጎች ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ስዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ