1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አርሜኒያ በካራባህ ስልታዊ ከተማን ሰጠች

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 17 2013

ናጎርኖ - ካራባህ ተራራማ ስፋራ በአርሜንያ እና በአዘርባጃን መካከል በተቀሰቀሰዉ ጦርነት አርሜኒያ ናጎርኖ-ካራባህ ክልል የሚገኘዉን  ስልታዊ ከተማን አሳልፋ መስጠትዋ ተዘገበ። ባኩ የሚገኘዉ የአዛርባጃን መንግሥት ናጎርኖ ካራባህ ተራራማ ስፍራ የምትገኘዉን ኩባዲ ከተማን መረከቡን አረጋግጦአል።

https://p.dw.com/p/3kVgG
Aserbaidschan | Berg-Karabach | Zerstörtes Haus in Tartar
ምስል Aziz Karimov/AP Photo/picture-alliance

ናጎርኖ - ካራባህ ተራራማ ስፋራ በአርሜንያ እና በአዘርባጃን መካከል በተቀሰቀሰዉ ጦርነት አርሜኒያ ናጎርኖ-ካራባህ ክልል የሚገኘዉን  ስልታዊ ከተማን አሳልፋ መስጠትዋ ተዘገበ። ኩባዲ የተሰኘዉ እና ከካራባህ ተራራማ ስፍራ ጋር ከሚያያዘዉ የኢራን አዋሳኝ በሆነዉ ቦታ ላይ የሚገኘዉ ከተማ ተላልፎ የተሰጠዉ አላስፈላጊ ጥፋትን ለማስወገድ ነዉ ሲል የአርመኔንያ መንግሥት መዲና የረቫን ላይ ዛሬ ገልፆአል። ባኩ የሚገኘዉ የአዛርባጃን መንግሥት ናጎርኖ ካራባህ ተራራማ ስፍራ የምትገኘዉን ኩባዲ ከተማን መረከቡን አረጋግጦአል። ይህ ርምጃ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አማካኝነት የተደረሰዉ የተኩስ አቁም ስምምንነት ተግባራዊ አለመሆኑን አመላካች ነዉ ተብሎአል።     

 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ