1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አምስቱ የዶይቼ ቬለ የፊልም ልማት ድጋፍ መርሃ-ግብር አሸናፊ

ሐሙስ፣ ግንቦት 12 2013

አምስት ኢትዮጵያዊያን ፊልም ሠሪዎች ከስልሳ አመልካቾች መካከል ቀዳሚ በመሆን የዚህ ዓመት የዶይቼ ቬለ የፊልም ልማት ድጋፍ መርሃ ግብር አሸናፊ ሆነው ተመረጡ። የዶይቼ ቬለ አካዳሚ ከጀርመን የፊዴራል የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለተመረጡት ኢትዮጵያዉያን ለእያንዳንዳቸው የአስር ሺህ ዩሮ ድጋፍ አፅድቆላቸዋል።

https://p.dw.com/p/3tgPC
Bildkombo Filmemacher DW

አሸናፊዎቹ ቤዛ ኃይሉ፣ አብርሃም ገዛኸኝ፣ ድርብድል አሰፋ፣ ሕይዎት አድማሱ እና ሄኖክ መብራቱ

አምስት ኢትዮጵያዊያን ፊልም ሠሪዎች ከ ስልሳ አመልካቾች መካከል ቀዳሚ በመሆን የዚህ ዓመት የዶይቼ ቬለ የፊልም ልማት ድጋፍ መርሃ ግብር አሸናፊ ሆነው ተመረጡ። የዶይቼ ቬለ አካዳሚ ከጀርመን የፊዴራል የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለተመረጡት ፊልም ሠሪዎች ሥልጠና እና ለእያንዳንዳቸው የአስር ሺህ ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አፅድቆላቸዋል። ቤዛ ኃይሉ፣ አብርሃም ገዛኸኝ፣ ድርብድል አሰፋ፣ ሕይዎት አድማሱ እና ሄኖክ መብራቱ ለዚሁ ድጋፍ ማመልከቻ ካስገቡ ስልሳ ፊልም ሠሪዎች መካከል ያቀረቡት የረጅምና አጭር እንዲሁም የዘጋቢ ፊልም ንድፈ ሀሳባቸው የተመረጡ ናቸው። የዶይቼ ቬለ የፊልም ልማት የገንዘብ ድጋፍ ፊልም ለመሥራት የሚወዱትን ባለሙያዎች የመደገፍና በሙያው ውስጥ እንዲያድጉ ፍላጎት ያላቸውን የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው። DW አካዳሚ ይህንን ውድድር አድርጎ ባቀረቡት ንድፍ የተሻሉ ሆነው የተገኙትን ከመምረጡ በፊት ፊልም ሰሪዎችን አግኝቶ ዳሰሳ አድርጎ ነበር። አካዳሚው እንዲህ ያለው ድጋፍ የኢትዮጵያ ፊልም ሠሪዎች ፣ ፊልሞቻቸው ጭምር በአገር ውስጥና በውጪ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያስችላል ብሏል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ