1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አማራ ክልል የሠፈሩ ተፈናቃዮች አቤቱታ

ዓርብ፣ ጥር 28 2013

የሱዳን ታጣቂዎች የምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎችን በመያዛቸዉ ከ1800 በላይ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ ምድረ-ገነት በተባለዉ አካባቢ ሰፍረዋል።

https://p.dw.com/p/3oxIr
Äthiopien | Flüchtlingslager Chagni
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

የአማራ ተፈናቃዮች አቤቱታ

የሱዳን ታጣቂዎች ያፈናቀሏቸዉ የምዕራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች በቂ መጠለያ አለማግኘታቸዉን አስታወቁ። የሱዳን ታጣቂዎች የምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎችን በመያዛቸዉ ከ1800 በላይ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተፈናቅለዉ ምድረ-ገነት በተባለዉ አካባቢ ሰፍረዋል። ለተፈናቃዮቹ ጥያቄ አፋጣኝ መልስ መስጠት የሚገባቸዉ የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና የምዕራብ አርማጭሆ ባለስልጣናት እርስ በርስ እየተወቃቀሱ ነዉ። ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለዉ ቻግኒ በተባለዉ ከተማ አጠገብ የሠፈሩ ተፈናቃዮች በበኩላቸዉ በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል። የአማራ ባለስልጣናት ግን ለተፈናቃዮቹ ርዳታ እየሰጡ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ