1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኖርድ ስትሪም 1 የጋዝ ማመላለሻ ሥራዉን ጀመረ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2014

ኖርድ ስትሪም 1 የተባለዉ እና ከሩስያ ወደ ጀርመን የተዘረጋዉ የጋዝ ማመላለሻ ቧንቧ ለጥገና እና ፍተሻ ሥራ ተብሎ ከተዘጋ ከአስር ቀናት በኋላ ዳግም ስራን መጀመሩ ተዘገበ። ለዓመታዊ የቁጥጥር ስራ የተዘጋዉ የጋዝ ማመላለሻ ቧንቧ ከጥገና በኋላ ወደ ጀርመን ጋዝ ማመላስ መጀመሩን የገለፀዉ የኖርድ ስትሪም የጀርመን ዜና አገልግሎት ወኪል ነዉ።

https://p.dw.com/p/4EUOR
Deutschland Lubmin | Start der Wartungsarbeiten an Nord Stream 1
ምስል Jens Büttner/dpa/picture alliance

ኖርድ ስትሪም 1 የተባለዉ እና ከሩስያ ወደ ጀርመን የተዘረጋዉ የጋዝ ማመላለሻ ቧንቧ ለጥገና እና ፍተሻ ሥራ ተብሎ ከተዘጋ ከአስር ቀናት በኋላ ዳግም ስራን መጀመሩ ተዘገበ። ለዓመታዊ የቁጥጥር ስራ የተዘጋዉ የጋዝ ማመላለሻ ቧንቧ ከጥገና በኋላ ወደ ጀርመን ጋዝ ማመላስ መጀመሩን የገለፀዉ የኖርድ ስትሪም የጀርመን ዜና አገልግሎት ወኪል ነዉ።  ይሁንና ለአስር ቀናት ተዘግቶ የነበረዉ የጋዝ ማመላለሻ ቧንቧ ጋዝ እስኪሞላና ጋዙ ጀርመን እስኪደርስ ድረስ ጥቂት ቀናት ሊወስድ እንደሚችል ተነግሮዋል። ካለፈዉ ሰኔ ጀምሮ፣ የሩሲያ መንግሥት የሆነዉ ግዙፍ የጋዝ አምራች ኩባንያ ጋዝፕሮም ለጀርመን ያቀርበዉ የነበረዉን የጋዝ አቅርቦት ከግማሽ በላይ መቀነሱን ካስታወቀ በኋላ ነበር፤ በየዓመቱ ለሚከናወን የጥገና ሥራ ከ1200 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለውን የጋዝ ማመላለሻ የቧንቧ መስመር ለሁለት ሳምንታት ገደማ ሙሉ በሙሉ ዘግቶት የቆየዉ።

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ