1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ናይሮቢ፤ በፍንዳታ እና ተኩስ ጥቃት ደረሰ

ማክሰኞ፣ ጥር 7 2011

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በአንድ ሆቴል ላይ በተኩስ እና በፍንዳታ ጥቃት መድረሱን ፖሊስ አመለከተ። ፍንዳው እና ተኩስ እንደተሰማ ዱሲት የተሰኘው ሆቴል ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለማዳን ሸሽተው መውጣታቸው ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3Bbku
Kenia Angriff auf Hotel in Nairobi
ምስል Getty Images/AFP/S. Maina

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በአንድ ሆቴል ላይ በተኩስ እና በፍንዳታ ጥቃት መድረሱን ፖሊስ አመለከተ። ፍንዳው እና ተኩስ እንደተሰማ ዱሲት የተሰኘው ሆቴል ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለማዳን ሸሽተው መውጣታቸው ተገልጿል። ሆቴሉ የሚገኝበት ጎዳና ለፖሊስ እንቅስቃሴ እንዲያመች መዘጋቱን በትዊተር መልእክት ያሳወቀው የኬንያ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ሌላ አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙም አሳስቧል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች ጭስ ከሕንፃዎች ሲወጣ ማመልከታቸውን የጀርመን የዜና ወኪል ዘግቧል። በጥቃቱ የሞተ ሰው እንዳለ ማረጋገጥ ያልፈለገው የኬንያ ቀይ መስቀል በበኩሉ ባልደረቦቹ በስፍራው እንደሚገኙ በመግለፅ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘ ለመገናኛ ብዙሃን እንደሚያደርስ ለዜና ወኪል መግለፁንም አስታውቋል። ናይሮቢ በሚገኘው ዱሲት ሆቴል ስለደረሰው የፍንዳታ እና የተኩስ ጥቃት የሚያመለክቱ ዘገባዎች ከስፍራው መውጣቱን ተከትሎም ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ ቡድን አሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል። ከመቅዲሾ ሮይተርስ እንደዘገበው የቡድኑ ቃል አቀባይ ጥቃቱ መቀጠሉን እና ፈጻሚውም አሸባብ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሆቴሉ ውስጥ መሽገዋል በተባሉት ጥቃት አድራሾች እና ፖሊስ መካከል ፍጥጫው ቀጥሏል። የደረሰ ጉዳት እስካሁን አልተገለፀም። 

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ