ነዋሪዎችን ያፈናቀለው የአዋሽ ወንዝ ሙላት
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2013ማስታወቂያ
በየዓመቱ ከላይኛው ተፋሰሱ እስከ ታችኛው የአፋር ምድር ከባድ ጎርፍ በማስከተል ነዋሪዎችን የሚያፈናቅለው የአዋሽ ወንዝ ሙላት ዘንድሮም በላይኛው የወንዙ ተፋሰስ ብቻ ከ 1400 በላይ አባወራዎችን ማፈናቀሉ ተገለፀ።
በወንዙ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸው በሦስት ዞኖች የሚገኙ አራት ወረዳዎች ናቸውም ነው የተባለው።
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ነዋሪዎች እንደሚሉት ሁሌም በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለጉዳት የሚዳረጉት ገበሪዎች ዘንድሮም የእርሻ ማሳቸው ወድሟል ከቤት ንብረታቸውም ተፈናቅለዋል።
አዋሽ የተለመደው ጉዳት እንዳያደርስ ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን የገለጸው የኦሮሚያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የታሰበው ስራ አስቀድሞ በጣለ ዝናብ ባለመጠናቀቁ ዘንድሮም የወንዙ ሙላት ከ2 ሺህ 400 መቶ በላይ ሄክታር መሬት ሸፍኖ 1 ሺህ 495 አባወራዎችን አፈናቅሏል ብሏል፡፡
ሥዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ