ነብዩ መሐመድ እና አስተምህሯቸው
ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2011ማስታወቂያ
የነብዮ መሐመድ ልደት መውሊድ በመላው አለም በሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ ተከብሮ ውሏል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች እለቱን በፀሎት፣ በምስጋናና በሌሎች ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ልምዶች ነው ያከበሩት ። የእስልምና ሃይማኖት ሊቃውንት ሙስሊሞች የነብዮ መሐመድን ምሳሌነት ተከትለው ለሰላምና ፍቅር ቅድምያ ይሰጡ ዘንድ ያስተምራሉ፡፡ ታማኝነትና መልካም ምግባርም የነብዩና የምእመናኑ መገለጫዎች ናቸው ይላሉ፡፡ 1493 ኛው የመውሊድ በዓል በማስመልከት የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ በመቐለ አንዋር መስጊድ የእስልምና ሃይማኖት መምህር ሼህ ዓብዱልቃድር ሙስጠፋን ስለ ነብዩ መሐመድ ማንነት እና አስተምህሯቸው አነጋግሯቸዋል።
እነሆ ዘገባው
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ