1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ዉስጥ የታሰሩት ጋዜጠኞች አልተለቀቁም

ረቡዕ፣ ጥር 24 2015

የኢትዮጵያ መንግስት ሐይል መቐለ ተቆጣጥሮ በነበረበት 2013 ዓመተምህረት ላይ ጠላት ከተባለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብረዋል በሚል 5 የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የታሰሩት ባለፈው ዓመት ወርሀ ግንቦት አጋማሽ ነበር።

https://p.dw.com/p/4Mz22
Äthiopien Oberster Gerichtshof von Tigray in Mekele
ምስል Million Hailesilassie/DW

ጋዜጠኞቹ የታሰሩት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብራችኋል ተብለዉ ነዉ

                       

 

የትግራይ ባለስልጣናት ከ8 ወራት በፊት ያሰሯቸዉን ሁለት ጋዜጠኞች እንዲለቅቁ የሚቀርበዉ ጥያቄና የሚደረገዉ ግፊት አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።ጋዜጠኛ ሃይለሚካኤል ገሰሰ እና ጋዜጠኛ ዳዊት መካነን የተባሉት የቀድሞ የትግራይ ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ከሌሎች አምስት ጋዜጠኞች ጋር የታሰሩት ጠላት ይበል ከነበረዉ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባራችኋል ተብለዉ ነበር።ዓለም አቀፉ የጋጤቸኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ CPJ በቅርቡ እንዳስታወቀዉ ሶስቱ ጋዜጠኞች ተለቅቀዋል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ እንደዘገበዉ ግን ሁለቱ ጋዜጠኞች  እስከ ዛሬ አልተፈቱም።

የኢትዮጵያ መንግስት ሐይል መቐለ ተቆጣጥሮ በነበረበት 2013 ዓመተምህረት ላይ ጠላት ከተባለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብረዋል በሚል 5 የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የታሰሩት ባለፈው ዓመት ወርሀ ግንቦት አጋማሽ ነበር። ተሾመ ጠማለው፣ ምስግና ስዩም፣ ሓበን ሓለፎም፣ ሃይለሚካኤል ገሰሰ እና ዳዊት መኮነን ከተባሉ ከነዚህ የቀድሞ የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች መካከል ሶስቱ ማለትም ተሾመ ጠማለው፣ ምስግና ስዩምና ሓበን ሓለፎም ከስምንት ወር እስር በኃላ በቅርቡ በፍርድቤት ትእዛዝ ነፃ የተለቀቁ ሲሆን ሌሎች ሁለቱ ጋዜጠኞች ሃይለሚካኤል ገሰሰ እና ጋዜጠኛ ዳዊት መኮነን ግን ከተዋጊ ሀይሎቹ የሰላም ስምምነት በኃላም ቢሆን የተከሰሱበት ከጠላት ጋር መተባበር የሚል ክስ በእስር ላይ ሆነው እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። 

 

የጋዜጠኛ ሃይለሚካኤል ገሰሰ ጠበቃ አቶ አብርሃ ካሕሳይ እንደገለፁልን  አሁን ላይ ደንበኛው የቀረበው የዓቃቤ ሕግ ክስ እና ምስክርነት የመከላከያ ሂደት ላይ መሆኑ ያነሱ ሲሆን በእስካሁኑ የደንበኛቸው እና ሌሎች ጋዜጠኞች የስምንት ወር የእስር ሂደት ግን በርካታ የሕግ እና ስነስርዓት ጥሰቶች መፈፀማቸው ገልፀዋል። በዚሁ የሁለቱ ጋዜጠኞች እስር እና ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ዙርያ ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ መረጃ ለማግኘ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ