1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ክልል በመቶ ሺህዎች ደሞዝ አልተከፈላቸውም 

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 4 2013

ትግራይ ክልል በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የክልሉ እና ፌደራል መንግስት ሠራተኞች እንዲሁም ጡረተኞች ለወራት ወርሐዊ ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸው ተገለጠ። እነዚህ የመንግስት ሠራተኞች እና ጡረተኞች ለከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ገልጠዋል።

https://p.dw.com/p/407cb
Äthiopien Tigray-Provinz Mekele
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ገልጠዋል

በትግራይ ክልል የሚገኙ 100 ሺህ ጡረተኞችን ጨምሮ ሌሎች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የክልሉ እና ፌደራል መንግስት ሠራተኞች ለወራት ወርሐዊ ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸው ተገለጠ። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት መዝጋታቸውን ተከትሎ ደሞዛቸው ያልተከፈላቸው እነዚህ የመንግስት ሠራተኞች እና ጡረተኞች ለከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ገልጠዋል። የሰላም ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ጌዜ በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት መዋቅር የለውም ብሏል።


ሚሊዮን ኃይለሥላሴ


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ