ትግራይ፤ ለተፈናቃዮች የገቢ ማሰባሰብያ
ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2011ማስታወቂያ
የክልሉ መንግስት በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ለማገዝ መዘጋጀቱ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረፅዮን ገልፀዋል፡፡ እንደ ክልሉ ሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፃ ባለፉት ሶስት ዓመታት በሀገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ19 ሺህ በላይ ቤተሰብ መሪዎች ተፈናቅለው ወደ ትግራይ ክልል መጥተዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች ለማገዝ 1 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ የትግራይ ክልል ሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልፅዋል፡፡
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ