1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት የሚሻው የእናቶች ሞት

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2012

በተመድ የምዕተአመቱ የልማት ግብ በተለይ በአፍሪቃ ሃገራት የእናቶችን ሞት በ75 በመቶ ለመቀነስ ታልሞ፤ ኢትዮጵያም ያንን ለማሳካት እየሠራች መሆኑን ታመለክታለች። ዛሬም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ  ከወሊድ ጋር በተገናኘ በዓመት 12 ሺህ እናቶች ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ባለሙያዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3XbuH
Symbolbild Afrika Schwanger
ምስል imago/i Images/A. Parsons

«የጤናማ እናትነት ወር ግንዛቤ በድሬደዋ»

ከወሊድ ጋር በተገናኘ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር እንዲቀንስ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይነገራል። በተመድ የምዕተአመቱ የልማት ግብ በተለይ በአፍሪቃ ሃገራት የእናቶችን ሞት በ75 በመቶ ለመቀነስ ታልሞ፤ ኢትዮጵያም ያንን ለማሳካት እየሠራች መሆኑን ታመለክታለች። ዛሬም ግን ኢትዮጵያ ውስጥ  ከወሊድ ጋር በተገናኘ በዓመት 12 ሺህ እናቶች ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለእናቶች ሞት መንስኤ ከሆኑ ዋና ምክንያቶች ግንባር ቀደሙ ደም መፍሰስ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ ደግሞ በርካታ እናቶች በገጠርም ሆነ በከተማ በቤት ውስጥ በመውለዳቸው ምክንያት የሚያጋጥም መሆኑ ነው የሚገለፀው። እንዲህ ያለውን እና በሰለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች ርዳታ ለመከላከል የሚቻለውን በወሊድ ጊዜ በያጋጥመው የደም መፍሰስ የሚደርሰውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ በጤና ተቋማት መውለድ ይመከራል። የድምጽ ቅንብሩ «የጤናማ እናትነት ወርን» አስመልክቶ በድሬደዋ ያለውን እንቅስቃሴ ያስቃኛል። ከድሬደዋ ዘጋቢያችን መሳይ ተክሉ አዘጋጅቶታል።

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ