1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትኩረት በአፍሪካ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 19 2013

የዓለም ጤና ድርጅት በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለማምረት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱን ባለፈው ሰኞ አስታውቋል። እርምጃው በአፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን ለማዳረስ ያለመ ነው። ባለፈው ረቡዕ በሊቢያ ቀውስ ላይ ያተኮረ ስብሰባ በበርሊን ተደርጓል። ትኩረት በአፍሪካ በሁለቱ አጀንዳዎች ላይ አተኩሯል

https://p.dw.com/p/3vbl8
Kuba Havana Coronavirus Lockdown
ምስል YAMIL LAGE/AFP via Getty Images

ትኩረት በአፍሪካ

የዓለም ጤና ድርጅት በደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለማምረት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱን ባለፈው ሰኞ አስታውቋል። እርምጃው በአፍሪካ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን ለማዳረስ ያለመ ነው። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንደገለጹት አፍሪጂን ባዮሎጂክስ የተባለ የክትባት አምራች ኩባንያ የሚሳተፍበት ነው። ኩባንያው ክትባቱን ከማምረት ባሻገር ስልጠና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው ረቡዕ በሊቢያ ቀውስ ላይ ያተኮረ ስብሰባ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ተደርጓል። ስብሰባው የዓለም ኃያላን እና የቀጠናው አገሮች ተወካዮች የተሳተፉበት ነበር።

 

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ