ተፈናቃዮቹ ተመለሱ
ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2011ማስታወቂያ
ሲዳማ ዞን ለክልልነት «ዘር ቆሌ» የገደለችዉን ቀብራ፣ ያቆሰለችዉን አስታማ አሁን ደግሞ ተፈናቃዮችዋን ወደየቤት ቀያቸዉ ለመለስ አንድ-ሁለት እያለች ነዉ። ካለፈዉ ሐምሌ 11 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ዞኑን ያወከዉን ግጭትና ግድያን ሸሽተዉ በተለይ ሁላ ከተባለዉ ወረዳ ተፈናቅለዉ ምስራቅ ጉጂ ዞን ሰፍረዉ የነበሩ ከ900 በላይ ነዋሪዎች ወየቀያቸዉ ተመልሰዋል። የወረዳዉ ባለስልጣናት እንዳሉት ለተመላሾቹ የዕለት ደራሽ ርዳታ ተሰጥቷቸዋልም። ይሁንና የአብዛኞቹ ተመላሾች ከብቶች፤ እና ሌሎች ሐብት ንብረቶች በመዘረፉና ቤቶቻቸዉ በመጋየቱ መልሶ መቋቋሙ ከባድ እንደሚሆንባቸዉ ተመላሾቹ እየተናገሩ ነዉ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ