1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባለሥልጣናት እገታ በአዊ ዞን 

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2010

የአዊ ዞን ነዋሪዎች የዞኑን አመራር አባላት እና የፀጥታ ኃይላትን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጋቸው ተሰማ። ነዋሪዎቹ የዞኑን አመራር አባላት እና የጸጥታ ኃይሎችን ባለፈው ቅዳሜ ወደ አላዥ ከተማ በመጡበት አጋጣሚ ነበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረጉት።ፖሊስ ሰዎቹን ለቆቿዋል ከተባለ በኋላ በተነሳ ግጭት4 ሰዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/31b0R
Karte Äthiopien englisch

የመሠረተ ልማት ግንባታ ጥያቄአችን ተገቢ ምላሽ አላገኘም ሲሉ በአማራ ክልል በአዊ ዞን ዚገም ወረዳ ቅላዥ ከተማ ነዋሪዎች የዞኑን አመራር አባላት እና የፀጥታ ኃይላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለፖሊስ ማስረከባቸው ተሰማ ። ነዋሪዎቹ የዞኑን አመራር አባላት እና የጸጥታ ኃይሎች ባለፈው ቅዳሜ ነበር ወደ አላዥ ከተማ በመጡበት አጋጣሚ ነበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረጉት። ፖሊስ ከነዋሪዎቹ የተረከባቸውን ሰዎችለቆቿዋል ከተባለ በኋላ በተነሳ ግጭት ፖሊሶች ተኮሱት በተባለው ጥይት 4 ሰዎች መቁሰላቸውን  ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ህዝቡን እናስተባብራለን ያሉ የዓይን ምስክሮች ገልጸዋል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ