1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተሐዋሲያንና ክትባቶች

ማክሰኞ፣ የካቲት 9 2013

ምድራችን በያዝነው ጎርጎርዮሳዊ ዓመት 2021 የካቲት ወር ከተመድ በወጣ የግምት መረጃ መሠረት 7,8 ቢሊየን ሕዝብ ይኖርባታል። በአንጻሩ በመላው ዓለም ከ30 ቢሊየን የሚበልጡ ተሐዋስያን እንዳሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ስለተሐዋሲዎች ምን ያህል እናውቃለን? ስለወቅቱ አነጋጋሪ ወረርሽኝ ኮቪድ 19ስ?

https://p.dw.com/p/3pRwy
Nachweis Coronavirus im Labor Symbolbild
ምስል picture-alliance/AP Photo/A. McAvoy

ስለተሐዋሲያን ክፍል አንድ ቃለ መጠይቅ

ባለፉት 13 ወራት ዓለምን ሰቅዞ የያዘው የኮሮና ተሐዋሲ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ ከሁለት ሚሊየን አራቶ መቶ በላይ ሰዎችን ሕይወት እንደዋዛ ቀጥፏል። የተሐዋሲው መዛመት ብቻ ሳይሆን ይከላከለዋ የተባለው ክትባት ዝግጅትና አቅርቦቱም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል። ተሐዋሲው በቻይና አንዲት ግዛት ተከስቶ ድንገት ዓለምን ያዳረሰ አደገኛ ብቻ ሳይሆን ዓለምን ከባድ ችግር ውስጥ የከተተ ወረርሽኝ ከሆነ አንድ ዓመት አለፈው። የኤኮኖሚም ሆነ የህክምና ምርምር አቅም ያላቸው ሃገራት ሳይቀሩ በዚህ የጤና ችግር ከባድ ፈተና ውስጥ ናቸው። በዓለማችን በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ ተሐዋስያን ነበሩ፤ ዛሬም አሉ። ስለተሐዋሲያን ምንነትና ባህሪ ምን ያህል እናውቃለን? 

ዶክተር ስንታየሁ አሰፋ ይባላሉ። በጀርመን ሀገር ላይፕዚሽ ከተማ ሄሊዮን ክሊኒክ በተባለ የጤና ተቋም የውስጥ ህክምናና በተሐዋሲያን የሚመጡ በሽታዎች ህክምና ዘርፍ ባለሙያ ናቸው።  በተሐዋስያን ላይ ከፍተኛ ምርምር በማካሄድ ባላቸው እውቀትም በተጠቀሰው ክፍል በከፍተኛ ደረጃ አማካሪ ሆነው ያገለግላሉ።   ይህን ጥያቄ ያነሳሁላቸው ዶክተር ስንታየሁ ብዛታቸው ከዓለም ሕዝብ ቁጥር በብዙ እጥፍ ይበልጣ ነው የሚሉት። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ