1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቦን፥ ለተፈጥሮ ጥበቃ ትኩረት ሰልፍ

ዓርብ፣ መስከረም 9 2012

ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ መንግሥታት ለተፈጥሮ ጥበቃ የሰጡት ትኩረት አናሳነት በመቃወም በተካሄደው ሰልፍ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የበርካታ ሃገራት ነዋሪዎች ተሳታፊ ኾኑ። የተቃውሞ ሰልፉን የጀመረችው አውስትራሊያ ስትኾን፤ እንደ ተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች ከኾነ ቢያንስ 300.000 ሰው በተቃውሞው ተሳታፊ ኾኗል።

https://p.dw.com/p/3PyDy
Kenia| Klimastreik | Global Strike 4 Climate | Nairobi
ምስል DW/A. Wasike

ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ መንግሥታት ለተፈጥሮ ጥበቃ የሰጡት ትኩረት አናሳነት በመቃወም በተካሄደው ሰልፍ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የበርካታ ሃገራት ነዋሪዎች ተሳታፊ ኾኑ። የተቃውሞ ሰልፉን የጀመረችው አውስትራሊያ ስትኾን፤ እንደ ተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች ከኾነ ቢያንስ 300.000 ሰው በተቃውሞው ተሳታፊ ኾኗል። በታይላንድ፤ ሕንድ እና ደቡብ ኮሪያም ተማሪዎች፣ እንዲሁም የሰልፉ ደጋፊዎች ተሳታፊ ኾነዋል። በርሊን ከተማ ውስጥ በተደረገው የከባቢ አየር ጥበቃ የተቃውሞ ሰልፍ 80.000 ሰዎች መሳተፋቸው ተገልጧል። ቦን የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ሠራተኞችም ዶይቸ ቬለ ከሚገኝበት ሕንጻ አቅራቢያ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ተከናውኗል። በመላው ዓለም ዙሪያ በዛሬው ዕለት ከ5000 በላይ የተቃውሞ ሰልፎች መከናወናቸው ታውቋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ