1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቦቦረና ከፍቶ በቀጠለው ድርቅ የተፈተነው ማህበረሰብ

ዓርብ፣ ጥር 19 2015

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ የተመታዉ አካባቢ ነዋሪ ህይወትን ለሚያሰጋ ረሐብ መጋለጡን ነዋሪዎችና ባለስልጣናት አስታወቁ ።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ለተከታታይ አምስት ወቅቶች ዝናብ በመሳቱ የሕዝቡ ዋና መተዳደሪያ የሆኑት ከብቶች በብዛት አልቀዋል።ሕዝቡ አስቸኳይ ድጋፍ ካላገኘ ረሐብና ረሐብ የሚያስከትለዉ በሽታ የሰዉ ሕይወት ማጥፋቱ አይቀርም።

https://p.dw.com/p/4Mo0d
Südostäthiopien | Dürre in Borena
ምስል Seyoum Getu/DW

«ባለን መሬት ዘርተን ቢያንስ ለቀለባችን አናጣም ነበር፡፡ አሁን የሚታረስ የለም፡፡ መሬቱ ደርቋል»

               
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ የተመታዉ አካባቢ ነዋሪ ህይወትን ለሚያሰጋ ረሐብ መጋለጡን ነዋሪዎችና ባለስልጣናት አስታወቁ ።ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ለተከታታይ አምስት ወቅቶች ዝናብ በመሳቱ የሕዝቡ ዋና መተዳደሪያ የሆኑት ከብቶች በብዛት አልቀዋል።ሕዝቡ አስቸኳይ ድጋፍ ካላገኘ ረሐብና ረሐብ የሚያስከትለዉ በሽታ የሰዉ ሕይወት ማጥፋቱ አይቀርም።

“በቦረና ዞን ያለው የድርቅ ተፅእኖ አስጊ ነው፡፡ አምና ስለ ከብቶች እልቂት ስናወራ ነበር፡፡ አሁን ግን ከዚያም ከፍቶ የሰው ነፍስም ወደ መጥፋቱ እያመራ ነው፡፡ ከአምናም እስካሁን ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የከብቶች እልቂት ከባለፈው ከፍቶ ነው የቀጠለው፡፡ የሰው ልጅ የሚቀመስ አጥተው ለህይወታቸው እየሰጉ ነው ያሉት፡፡”
ይህን አስተያየት ያጋሩን በቦረና ዞን የተልተሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት መምህር ዱባ ቡራ  ናቸው፡፡ በዚሁ ወረዳ ዲቤ ጋያ ቀበሌ የሚኖሩ ሌላው 18 የቤተሰብ አባላትን ሲያስተዳድሩ የነበሩት አርብቶ አደር ማሊቻ ሞሌ አሁን እጆቻችንን አጣጥፈን ለመቀመጥ ተገደናል ይላሉ፡፡ “ድሮ ባለን መሬት የሆነ ነገር ዘርተን ቢያንስ ለቀለባችን አናጣም ነበር፡፡ አሁን የሚታረስ የለም፡፡ መሬቱ ደርቋል እህል አያበቅልም፡፡ ከከብቶቻችን ቀረን ምንለው የለም፡፡ አሁን ተስፋ ቆርጠን የችግር የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ካሉኝ የበተሰብ አባላት ያልተራበ ማንም የለም፡፡ እንደውም ሶስቱ የቤተሰቦቼ አባላት በዚሁ ተማረው እግራቸው ወዳመራቸው ሄደዋል፡፡ አሁን ሰው በርሃብ ወደ መሞቱ ነው፡፡ አሁን እዚሁ ጎረቤተ ርሃብ በሚመስል መልኩ ሰው ሞቶ እዛ እያስተዛዘን ነው፡፡” 
ዴንጌ ዋሪዮ ደግሞ የዚህች ቀበሌ አስተዳዳሪ ናቸው፡፡ “ታውቃለህ በድርቁ ሰው የካፋ ችግር ውስጥ ነው ያለው፡፡ ያላቸው ከብቶች በግ እና ፍየል እንኳ ሳይቀር አልቀዋል፡፡ ጠብ ያለ ዝናብ ባለመኖሩ የሚወጣ እህል የለም፡፡ የሚሸጥ ከብት በሙሉ በድርቁ አልቀዋል፡፡ አሁን ሰው በችግሩ በህይወት እስከማለፍ ደርሷል፡፡ የሚቀመስ በመጥፋቱ በዚሁ ዓመት ብቻ በዚህች ቀበሌያችን አራት ሰው የሚደርስ ተጎሳቅለው አልፈዋል፡፡ አሁን የሞቱት መጀመሪያ ሰውነታቸው ያብጣል፡፡ ከዚያን ምንም አይነት ምግብ መውሰድ ተስኖያቸው ተጎድተው ይሞታሉ” ሲሉ አስቸጋሪ ያሉት ማህበረሰቡ ያለበትን ችግር አብራርተዋል፡፡
ዶይቼ ቬለ በዚህች ተልተሌ ወረዳ እንዲሁም በቦረና ዞን የአደጋ ስጋት ስራ አመራሮች እና የጤና መምሪያ ባለስልጣናት ጋር እንዲሁም የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ኃላፊዎች ጋ በመደወል ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ 
ላለፉት አምስት የዝናብ ወራት ቦረና ምንም አይነት ዝናብ እንዳላገኘ የሚያነሱት የዞኑ እንስሳት ሃብት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ቃሲም ጉዮ እንደሚሉት ግን በከፋ ሁኔታ የቀጠለው ይህ ድርቅ በዞኑ ካሉት 7.2 ሚሊየን የእንስሳት ሃብት ከቤት እንስሳት ብቻ 2.3 ሚሊየን ያህሉ አልቀዋል ባይ ናቸው፡፡ 
ከዚህ በፊት በቦሬና ከፊል ወረዳዎች ድርቅ ሲመታቸው በከፊል ወዳሉ በመንቀሳቀስ አርብቶ አደሩ የራሱን እና የከብቶቹን ህይወት እንደሚታደግም በመግለጽ አሁን ግን ሁሉም የዞኑ አከባቢዎች ያውና አንድ መሆኑ ማህበረሰቡን ማምለጫ አሳጥቶታል ብለዋል ሃለፊው፡፡ 
የቦረና ህዝብ እርሰ በርስ በመረዳዳት ባህላዊ እሴቱ እና መንግስትም በሚያደርገው ድጋፍ ህይወቱን እስካሁን ማቆየት መቻሉንም በመግለጽ አሁን ግን የከፋ ችግር ማህበረሰቡን እንደሚጠብቀውም አንስተዋል፡፡
ይሄው ለአምስት የዝናብ ወቅት ወራት ሰፍኖ የቆየው ድርቅ ከዞኑ ህዝብ ከ600-800 ሺህ  የሚገመት ቁጥር ያላቸው ለከፋ ስቃይ እንዲዳረጉ ማድረጉ ነው የሚነገረው፡፡ በዞኑ እስካሁን ባለቁት 2.3 ሚሊየን በሚገመት የዞኑ እስሳት ሃብት 22 ቢሊየን ብር የሚገመት ሃብትን ማሳጣቱም ነው የተገለጸው፡፡ ከቤት እንስሳት በተጨማሪም አሁን አሁን የዱር እንስሳትም ድርቁን መቋቋም ተስኗቸው በስፋት እያለቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የቦረና አርብቶ አደሮች ድርቁን በመሸሽ ቀን ቢያልፍ ብለው ከአርሲ እስካ ጂንካ እና ጋሞ ዞን ድረስ የተወሰነውን የከብቶቹን ዝርያ እንኳ ለማትረፍ ከቀዬው ተሰዶም ይገኛሉ ተብሏል፡፡ 

Äthiopien | Dürre in Borena
ቦረና ዞን ድርቁ ከፍቷልምስል Firaol Wako/PHD
Äthiopien | Dürre in Borena
ቦረና ዞን ድርቁ ከፍቷልምስል Firaol Wako/PHD

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ 

ታምራት ዲንሳ