1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቦሪስ ጆንሰን ወደ ሥራቸዉ ተመለሱ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 19 2012

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኒያቸዉ የተቋቋመዉና  በሃገሪቱ የሚታየዉን የኮሮና ቀዉስን የሚከታተለዉን ኮሚቴ እንደሚመሩ ተዘግቦአ። በብሪታንያ በኮሮና የሚያዘዉም ሆነ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዘርፍ ባለሞያዎችና የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃገሪቱ ያወጣችዉን ሕግ ማላላት እንደሚገባ እየወተወቱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3bUKj
Großbritannien Boris Johnson
ምስል picture-alliance/dpa/S. Rousseau

ከኮሮና ተኅዋሲ ሕመም ያገገሙት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራቸዉ እንደተመለሱ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ትናንት እሁድ ምሽት ቢሮአቸዉ ተገኝተዉ እንደነበር አንዲንት የብሪታንያ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታዉቃለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካቢኒያቸዉ የተቋቋመዉና  በሃገሪቱ የሚታየዉን የኮሮና ቀዉስን የሚከታተለዉን ኮሚቴ እንደሚመሩ ተዘግቦአ። በብሪታንያ የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭትን ተከትሎ በተኅዋሲዉ የሚሞተዉና ፤ የሚታመመዉ ሰዉ ቁጥር አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ዘርፍ እና የመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሃገሪቱ አዉጥታዉ የነበረዉን የዝዉዉር ሕግን ማላላት እንደሚገባ እየወተወቱ ነዉ። የዩናይትድ ስቴትሱ የተኅዋሲዎች ጉዳይ ጥናት ተቋም ጆን ሆፕኪንስ ይፋ በአደረገዉ መሰረት ፤ በብሪታንያ 153 ሺህ ሰዎች በኮሮና ተሕዋሲ ተይዘዋል፤  20, 732 ሰዎች ደግሞ ኮሮና ባስከተለዉ ሕመም ሞተዋል።    

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ