1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሔራዊ የሥነ-ልክ እና የልኬት ደረጃ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ጥራትን ለማስጠበቅ ፣ ደረጃንም በዓለም አቀፍ ልኬት መሰረት ለማስኬድ አራት የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማትን አቋቁማለች ። እነዚህም የኢትዮጵይም ደረጃዎች ኤጀንሲ ፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ኢንተርፕራይዝ፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት እና ብሔራዊ የሥነ ልክ ኢንስቲቲዩት ናቸው።

https://p.dw.com/p/3Vtl5
Äthiopische nationale Mess-Standards, Kalibrierung und zertifizierte wissenschaftliche Materialien
ምስል DW/S. Muchie

ብሔራዊ የሥነ-ልክ እና የልኬት ደረጃ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ጥራትን ለማስጠበቅ ፣ ደረጃንም በዓለም አቀፍ ልኬት መሰረት ለማስኬድ አራት የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማትን አቋቁማለች ። እነዚህም የኢትዮጵይም ደረጃዎች ኤጀንሲ ፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ኢንተርፕራይዝ፣ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት እና ብሔራዊ የሥነ ልክ ኢንስቲቲዩት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የሆነው ብሔራዊ የሥነ ልክ ኢንስቲቲዩት ሃገራዊ የልኬት ደረጃ ተዋረድን የመጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል። በተጨማሪም የካሊብሬሽን ፣በጤና ፣ በግንባታ ፣ በኢንዱስትሪ ፣ በኤሌክትሪክና በሌሎች የሳይንስ መሳሪያዎች ላይም የጥራት ደረጃን ከመፈተሽ በተጓዳኝ የጥገና አገልግሎትም ይሰጣል። ከዚሁ መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በሥነ-ልክ ፍተሻ ከፍተኛ ጉድለት የሚታይባቸው በከፍተኛ ወጪ የሚገዙ የመንግስትና የህዝብ ሐብት የሆኑ ውድ መሳሪያዎች በየተቋማቱ በአቧራ ተውጠው ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የታወቀ የጊዜ ልኬት ደረጃ የላትም። በታመሳሳይ በሃገሪቱ የኬሚካል ሥነ -ልክ ስራም እስካሁን አልተጀመረም። ሌላው ቀርቶ ርዝመትን በክንድ፣ ስፋትን በገመድ፣ የእህል ግብይትን በጣሳ እና ቁና መለካትም ሙሉ በሙሌ ቀርቷን ማለት አይቻልም። ይህ ደግሞ ሳይንሳዊ ልኬትን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር በሚፈለገው ውጤት ላይ የሚያሳርፈው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሥነ-ልክ እና የልኬት ደረጃ ምን ይመስላል? ሙሉ መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ