1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባቸሌት በትግራይ ምርመራ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

ሐሙስ፣ መጋቢት 9 2013

ትግራይ ዉስጥ ሕግን ማስከበር የተባለዉን ዘመቻ ተከትሎ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ ጥሰቶችን ለማጣራት ኢትዮጵያ ያቀረበችዉን በጋራ የማጣራት ጥያቄ መቀበሉን የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3qpVG
Michelle Bachelet | UN Hochkommissarin für Menschenrechte
ምስል picture-alliance/Keystone/S. Di Nolfi

ትግራይ ዉስጥ ሕግን ማስከበር የተባለዉን ዘመቻ ተከትሎ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ ጥሰቶችን ለማጣራት ኢትዮጵያ ያቀረበችዉን በጋራ የማጣራት ጥያቄ መቀበሉን የመንግሥታቱ ድርጅት ጽ/ቤት አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ሃላፊ ሚሼል ባቼሌትን ጠቅሶ የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ እንደዘገበዉ፤ በትግራይ ተፈፀመ የተባለዉን የመብት ጥሰት በጋራ ለማጣራት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበዉ በጋራ የማጣራት ጥያቄ ላይ ተስማምተዋል። ዜና አገልግሎቱ  ዛሬ እንደዘገበዉ፤ የፀጥታ ኃይሎች በትግራይ የጅምላ መጨፍጨፋ፣ የጾታ ጥቃት እና ግድያ በሰፊዉ መፈፀማቸዉን የክልሉ ነዋሪዎች ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የእርዳታ ሰራተኞች የትግራይ የጤና ስርዓት በአብዛኛው መዉደሙን እና በክልሉ መጠነ ሰፊ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቃቸዉንም ዘግቦአል። የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሽን በትግራይ ያለዉን ሁኔታ በጋራ ማጣራት ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን «ኢሰመኮ» ለጽ/ቤቱ ላቀረበዉ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ መስጠቱን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት « UNHCR » ቃል አቀባይ ለፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ መግለፃቸዉ ተዘግቦአል። ይህን ተከትሎ  የመንግሥታቱ ጽ / ቤት የማጣራት ተልዕኮዉን በተቻለ ፍጥነት ለማስጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑም ተመልክቶአል።

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ