1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባልደራስ የመጀመርያውን ጉባኤ አካሄደ

ሰኞ፣ የካቲት 2 2012

ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፍትሃዊና ታማኝነት እንዲከናወን የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎች ገብተው እንዲከታተሉ ግፊት አደርጋለሁ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ገለጸ።

https://p.dw.com/p/3XZIB
Äthiopien Addis Abeba | Balderas-Partei während Generalversammlung
ምስል DW/S. Muche

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ


ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፍትሃዊና ታማኝነት እንዲከናወን የአውሮፓ ሕብረት ታዛቢዎች ገብተው እንዲከታተሉ ግፊት አደርጋለሁ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ገለጸ። ፓርቲው ትናንት የመጀመሪያ መስራች ጉባኤዉን ያከናወነ ሲሆን 60 የፓርቲው አመራሮችንና የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትን ስም ለጉባኤተኛው አስተዋውቋል። ጉባኤውን በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጽ/ቤት ያደረገው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ጉባኤውን ሌላ ቦታ እንዳያደርግ በከተማ አስተዳድሩ ክልከላ ተደርጎበታል በማለት የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ እስክንድር ነጋ ተናግረዋል።


ሰለሞን ሙጬ 


ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሠ