ባልደራስ በፓሪስ
ዓርብ፣ ነሐሴ 10 2011ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ወይም ባልደራስ የተባለዉ ስብስብ ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ በጠራዉ ስብሰባ ሰበብ ፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እየተወዛገቡ ነዉ።የባልደራስ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ለገሠ የተገኙበትን ትናንት የተደረገዉን ስብሰባ ያዘጋጁት ወገኖች በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምኒቲ) ለዝግጅቱ ሊተባበረን ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ወቀሱ። የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በበኩሉ ስብሰባዉ እንደሚደረግም ሆነ አቶ ኤርሚያስ እንደሚመጡ አስቀድሞ እንዳልተነገረው፣ የአዘጋጆቹ ማንነት እንዳልተገለጸለትም አስታዉቋል። በፓሪሱ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት አቶ ኤርሚያስ የአዲስ አበባ ህልውና እና ባለቤት ጉዳይ አደጋ ላይ ነው ማለታቸውን የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዘግባለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ