1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፓሪስ የኢትዮጵያዉያን ገና በዓል አከባበር

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2011

«ኢትዮጵያ ፈረንሳይ» በተሰኘ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን ዓመት የተቋቋመዉ ማኅበር በኢትዮጵያና ፈረንሳይ መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማጠናከር በድልድይነት እንደሚሰራ ተገለፀ።  ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የሚገኘዉ ይህ ማኅበር፤ አሳዳጊ የሌላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሕጻናት በጉዲፈቻ ወደ ፈረንሳይ መጥተዉ ባደጉ ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች የተቋቋመ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3B9NZ
Frankreich | Paris Skyline
ምስል Getty Images/Bloomberg/C. Morin

የፈረንሳይና የኢትዮጵያን ግንኙነት ለማጠናከር እየሰራን ነዉ


ማኅበሩ  በዋንኛነት በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል የባህል፤ የትምህርት እና የንግድ ትስስርን ለማጠናከር እንደድልድይ በመሆን የሁለቱን ሃገራት ትስስር ማጠናከር ብሎም ኢትዮጵያዊ ማንነትን ባህልን እና ታሪክን መፈለግን ዋናዉ ትኩረቱ ያደረገ ነዉ።  ማኅበሩ የዘንድሮዉን የኢትዮጵያን የገና በዓል ባሳለፉት ወራቶች ያደረጋቸዉን እንቅስቃሴዎች እና የፈረንሳይና የኢትዮጵያን የባህል ልዉዉጥን ለማጠናከር በሚል በፈረንሳይ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያዉያን እና ፈረንሳውያን ጋር በድምቀት አክብሮአል። ትናንት በገና በዓል ዋዜማ «ኢትዮጵያ ፈረንሳይ» ማኅበር መጠለያ ለሌላቸዉ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ ለሚገኙ ስደተኞች የእራት ግብዣም አድርገዋል። በዝግጅቱ ላይ የተገኘችዉ የፓሪስዋ ወኪላችን  ዝርዝር ዘገባዉን አዘጋጅታለች።    

 
ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ