1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ የቀጠለው ተቃውሞ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 29 2011

ፈረንሳይ ከሰሞኑ ተቃውሞ እየናጣት ነው። ባለፉት ቀናት በዋና ከተማዋ ፓሪስ አደባባይ ላይ  ቢጫ ሰደሪያ በሚል ስያሜ ተቃውሟቸውን ቢጫ ለብሰው ሲያስተጋቡ የሰነበቱት ዜጎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች እያከታተሉነው።

https://p.dw.com/p/39kAq
Frankreich Gelbwestenprotest in Paris
ምስል picture-alliance/AP Photo/T. Camus

አመፅ የቀላቀለ ተቃውሞ በፓሪስ

ተቃዋሚዎቹ ከፖሊስ ጋር የተጋጩ ሲሆን ሦስት ፖሊሶችን ጨምሮ  ከ30 በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፈረንሳይ ባለሥልጣናት 8,000 ሰዎች መሳተፋቸውን የገለጡ ሲሆን 600 ያህል መፈተሻቸውን እና ለአጭር ጊዜም ቢሆን በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቀዋል። በዛሬው ዕለትም ከተማዋ የተለመደ እንቅስቃሴዋ ርቋት እንደዋለች የገለፀችልን የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ፤ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ተቃውሞ ከሚያካሂዱት ፈረንሳውያን ጋር እንደሚነጋገሩ ባለስልጣናት ማመልከታቸውን ገልፃልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ