1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎንደር ዙሪያ ግጭት የሰዎች ሕይወት አለፈ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2012

አማኙ እንዳሉት ከባለፈው አርብ ጀምሮ “ቁስቋምና ዙሪያው፣ ደፈጫ፣ ሮቢት በተባሉ አካባቢዎች ግጭቶች ተፈጥረው ጉዳት ደርሷል፣ ትናንትና ደግሞ ፀዳ አካባቢ ሁለት ሰዎች ተገደለዋል፣ በደፈጫ ኪዳንምህረት፣ አንገረብ ማዶ፣ ወለቃ ላይም ቤቶች ተቃጥለዋል” ብለዋል፡፡አኝሁ የዓይን እማኝ እንደሚሉት ዛሬ ሌሊቱንም እረፍት የሌለው የጥይት ተኩስ ሲሰማ ነበር፡፡

https://p.dw.com/p/3RNif
Äthiopien Vertriebene aus Chilga
ምስል DW/A. Mekonnen

በግጭቱ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪዎችና ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ከመስከረም 18/1012 ዓ ም ጀምሮ አንዴ በረድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለው ግጭት ሰሞኑን በጎንደርና ዙሪያዋ ተባብሶ የሰው ህይወት መጥፋቱንና ቤቶች መቃጠላቸውን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል። አማኙ እንዳሉት ከባለፈው አርብ ጀምሮ “ቁስቋምና ዙሪያው፣ ደፈጫ፣ ሮቢት በተባሉ አካባቢዎች ግጭቶች ተፈጥረው ጉዳት ደርሷል፣ ትናንትና ደግሞ ፀዳ አካባቢ ሁለት ሰዎች ተገደለዋል፣ በደፈጫ ኪዳንምህረት፣ አንገረብ ማዶ፣ ወለቃ ላይም ቤቶች ተቃጥለዋል” ብለዋል፡፡ አኝሁ የዓይን እማኝ እንደሚሉት ዛሬ ሌሊቱንም እረፍት የሌለው የጥይት ተኩስ ሲሰማ ነበር፡፡ ግጭቱ ቀደም ሲል በአካባቢው “አማራና ቅማንት” በሚል ተነስቶ ከነበረው ግጭት እንደሚገናኝ ነው ያመለከቱት፡፡ከአራት ቀናት በፊትም አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ የሚገፋፋ ጽሁፍም በጎንደር ከተማ ተበትኖ መገኘቱን እማኙ ተናግረዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ለዶቼቬለ DW አንደገለፁት በጎንደር ዙሪያና  አካባቢዋ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን አረጋግጠዋል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የአማራ ተወላጆች አማራ በብዛት ወዳለበት አካባቢ፤ የቅማንንት ተወላጅ ነዋሪዎች ደግሞ የቅማንት ነዋሪዎች ወዳሉበት መፈናቀላቸውን አመልክተዋል፡፡በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት እንደጠፋ አቶ ተስፋ ቢናገሩም ቁጥሩን ለመግለፅ አልፈለጉም፡፡የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅድ ታቅዷል ያሉት አቶ ተስፋ አሁን ግጭቱን ለማብረድ የፀጥታ ኃይሉ እየተረባረበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡አንደነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በጉንደር ዙሪያ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች የጥይት ተኩስ በጎንደር ዙሪያ አካባቢዎች ይሰማል፡፡ባለፈው ዓመት ህዳር 2011 ዓ ም በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል፣ 6000 ያህል ቤቶች ተቃጥለዋል፣ 60 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ