1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰዎች ዝውውርና የኮሮና ስጋት በአማራ ክልል

ዓርብ፣ ግንቦት 14 2012

ችግሩ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።በዘጠኝ አካባቢዎች ለይቶ ማቆያ ቦታዎች እንዳሉ ዘጠኝ መቶ 56 ሰዎች ተለይተው የ236 ሰዎች ናሙና ተወስዶ 12 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3ccZw
Äthiopien - Gonder
ምስል DW/A. Mekonnen

በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ተህዋሲ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችሉ የአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ማህበራዊ ልማት መምሪያ አስታውቋል።የክልሉ ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100  እስከ 150 ሰዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ተህዋሲ የተገኘባቸው  ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም። የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ ለዶቼ ቬለ በስልክ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል:: በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል::ችግሩ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና  አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል::በዘጠኝ አካባቢዎች ለይቶ ማቆያ ቦታዎች እንዳሉ ዘጠኝ መቶ 56 ሰዎች ተለይተው የ236 ሰዎች ናሙና ተወስዶ 12 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል::የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፀዳለ ሰሙንጉስ በበኩላቸው ዋናው ችግር ከውጪ የሚገቡ ሰዎች ናቸው ብለዋል::የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት  ከሱዳንና ከጅቡቲ አካባቢዎች ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከፌደራል መንግስት ጋር በጋራ የምንፈታው ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል::በሽታውን ለሚከላከሉና የኮቪድ 19 ታማሚዎችን ለሚያክሙ የጤና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸውም ተገቢው ትኩረት በመንግስት እንዲሰጥም ኃላፊዋ ጠይቀዋል::

ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ
 

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ