1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዳይመንድ ሊግ የ3000 ሜትር ውድድር እጅጋየሁ ታዬ ሁለተኛ ወጣች

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 22 2013

በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉባቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ተካሒደዋል። በሶስት ሺሕ ሜትር በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ እጅጋየሁ ታዬ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው የቡሩንዲዋ ፍራንሲን ንዮንሳባ ነች።

https://p.dw.com/p/3zcHo
Frankreich Francien Niyonsaba und Ejigayehu Taye
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

ከሐይማኖት ጥሩነሕ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ዛሬ በጃፓን ቶኪዮ በፓራ ኦሎምፒክ በተካሔደ የ1,500 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት ገዛኸኝ አሸናፊ ሆናለች። ትዕግስት በፓራ ኦሎምፒክ ውድድር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ በማስገኘት የመጀመሪያዋ አትሌት ሆናለች።

ከዚያ በተጨማሪ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉባቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች ተካሒደዋል።

በሶስት ሺሕ ሜትር በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ እጅጋየሁ ታዬ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው የቡሩንዲዋ ፍራንሲን ንዮንሳባ ነች።

ውድድሩን የተከታተለችውን የዶይቼ ቬለ የፓሪስ ወኪል ሐይማኖት ጥሩነህን በስልክ ማብራሪያ ሰጥታለች።

ሐይማኖት ጥሩነሕ

እሸቴ በቀለ