1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሌራ 18 ሰዎች ገደለ

ዓርብ፣ ጥር 15 2012

ቢሮው ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ካለፈው ወር አጋማሽ አንስቶ አስራ ስምንት ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።።አንድ ሺህ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የሥራ ሃላፊዎች ቢሮው የጠቀሰው በኮሌራ የሞቱ እና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ትክክለኛ መሆኑን ለዶቼቬለ አረጋግጠዋል።

https://p.dw.com/p/3Wlp9
Bakterien Erreger der Cholera
ምስል picture-alliance/Dr.Gary Gaugler/OKAPIA

ኮሌራ 18 ሰዎች ገደለ

በደቡባዊ ኢትዮጵያ የሥርጭት አድማሱን ያሰፋው ኮሌራ ለህዝቡ ስጋት፣ለአገሪቱም ፈተና መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ አስታወቀ።ቢሮው ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ካለፈው ወር አጋማሽ አንስቶ አስራ ስምንት ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸው አልፏል።አንድ ሺህ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የሥራ ሃላፊዎች ቢሮው የጠቀሰው በኮሌራ የሞቱ እና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ትክክለኛ መሆኑን ለዶቼቬለ አረጋግጠዋል።የበሽታውን ሥርጭት ለመቆጣጠርም የክልሉ ጤና ቢሮ በቅንጅት በመረባረብ ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።የሃዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ