1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወታደሮች የተረሸኑ ወጣቶች ቤተሰቦች የፍትሕ ጩኸት

ሐሙስ፣ ሰኔ 1 2015

የመከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች ሁለት ግለሰቦችን እጃቸውን ወደኋላ የፊጥኝ አስረው ጫካ ውስጥ በጥይት ሲረሽኑ የሚያሳይ ተንቀሰቃሽ ምስል ከሰኞ ጀምሮ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወር ቆይቷል ። በርካታቶችን ያስቆጣው ይህ ዘግናኝ ድርጊት መቼ እና የት ነው የተፈጸመው?

https://p.dw.com/p/4SLKq
Äthiopien Benishangul Region, Stadt  Metekel
ምስል Negassa Dessakegen/DW

ይህ ዘግናኝ ድርጊት መቼ እና የት ነው የተፈጸመው?

የመከላከያ የደንብ ልብስ የለበሱ ወታደሮች ሁለት ግለሰቦችን እጃቸውን ወደኋላ የፊጥኝ አስረው ጫካ ውስጥ በጥይት ሲረሽኑ የሚያሳይ ተንቀሰቃሽ ምስል ከሰኞ ጀምሮ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወር ቆይቷል ። ይህ ዘግናኝ ድርጊት የሚታይበት የተንቀሳቃሽ ምስል በርካታቶችን አስቆጥቷል ። ከገዳዮቹ ወታደሮች መካከል የአንዱ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ላይ የታተመ የሲዳማ ክልል ባንድራ ይታያል ። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከማኅበረሰብ አንቂዎች አንስቶ እስከ ፖለቲከኞች ብሎም ግለሰቦችን እያወዛገበ ይገኛል ።  የሟች ቤተሰቦች ግድያው የተፈጸመው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ዓመት ጥር ወር 2014 ዓ.ም እንደሆነ ለዶይቸ ቬለ (DW)  ተናግረዋል።  

ባለፈው ዓመት ለተለያዩ ተቋማት   ሰብአዊ መብትን ጨምሮ አቤቱታ ቢቀያቀርቡም ፍትህ ማግኘት አልቻልነም ብሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትየጵ ሰብአዊ መብች ኮሚሽን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ እና ለጊዜው ማብራሪያ እንደማይሰጥ ጠቁመዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማበራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ እስካሁን ከመንግስት በኩል በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም፡፡

ከሰሞኑ በማህበራዊ መገናኛ ዜደዎች ላይ ሲዘዋወር የነበረው ወታደሮች  በጫካ ውስጥ ሁለት ግሰለቦችን ሲገድሉ የሚያሳይ የአንድ ደቂቃ ከአስራ ስድስት ሴኮንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል፡፡  በርካቶችም በማህበራዊ መገናኛ ዜደ ድርጊቱን እያወገዙ ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ጊጶ በሚትባል ቀበሌ ውስጥ መፈጸሙትን ያነጋገርናቸው የተጎጂ በተሰቦች አመልክተዋል፡፡ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች መካከል አንዱ ታከለ መንገሻ ዱጉማ  እንደሚባልም በዛው ድባጢ ወረዳ ጫንጮ የተባለ ቀበሌ ነዋሪ መሆኑን ከበተሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡  ሌላኛው ደግሞ አብታሙ አያና የተባሉ   እንደሆኑ ተገልጸዋል፡፡ 

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን

አቶ ታከለ መንገሻ በጥር ወር/2014 ዓ.፣ም በዕለት አርብ በማያውቁት ጉዳይ ተጠርጥሮ መያዙን ወንድሙ ለዲዳቢሊው አብራርተዋል፡፡ ከተያዙ በኃላም ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል መደብዱንና ወደ ማረሚያ እንወደሳቸዋለን በማለት ከስፍራው ይዘውት መውጣታቸውንና ጊጶ በተባለ ቦታ ጫካ ውስጥ ገድለው መጣላቸውን አብራርተዋል፡፡
በወቅቱ የተገደሉት ሌላው ወጣት ሀብታሙ አያና የመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ የጸጥታ ሀይሎች ተፈለጋለህ ብለው ከወሰዱት በኃላ ጋለሳ የተባለ ቀበሌና አንድ ያልታወቀ ስፍራ ለ3 ቀናት ታስሮ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ሀብታሙን ጨምሮ ሌሎች 2 የበተሰባቸው አባላት ባለፈው ዓመት 2014 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜ በደረሰባቸው ድብደባና ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን አክለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ሰሞኑን የተሰራጨውን ቪድዩ በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሚኝን እና ሲጣራ እንደሚገልጹ የኮሚሽኑ ባለሞያዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በኮሚሽኑ የሪጅናል ዳይረክተር የሆኑት አቶ ኢማድ አብዱልፈታህ በህግ የተያዙ ሰዎች መብት በሀገሪቱ ህገ መንግስት እና ኢትዮጵያ በተቀበላቻቸው አለም ዓቀም ህጎች የተካተቱትን አሰራሮች በመከተል   የተያዙ ሰዎች መብት መከበር አለበት ብሏል፡፡  

በተሰራጨው ቪዲዩ ላይ ወደ አራት ዩኒፎረም የለቡስ ወታደሮች የሚታዩ ሲሆን ከእነዚህም በአንዱ ዩኒፎረም ላይ የታተመ የሲዳማ ክልል ባንድራ ይታያል፡፡ የሲዳማ ክልል ሰላም እና ጸጥታ በሮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየዘዋወረ የሚገኘው መረጃ ፍጹም የስራዊቱን ዲስፒሊን የማያሳይና ከእውነታው የሚጻረር ነው ብሏል፡፡ ተመሳስሎ በተሰራው መለዩ የቀድሞውን ልዩ ሐይላችንን ስም ማጠልሸት አይቻልም ሲል በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ በተሰራጨው መግለጫው ጠቁመዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ባለፈው ዓመት ከኮማንድ ፖስት በተጨማሪ የአካባቢውን ሰላም ለማስከበር ሲባል የአራት ክልሎች ልዩ ሀይሎች ማለትም የጋምቤላ፣ የሲዳማ፣የደቡብ እና አማራ ክልል ልዩ ሀይሎች በቦታው ላይ ሰፍሮ እንደነበር ተወሳል፡፡

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሀመድ