1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የአረና ትግራይ መግለጫ

ማክሰኞ፣ የካቲት 10 2012

በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዓረና ትግራይ ለሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ እስር፣ አካላዊ ድብደባና ሌሎች ጥቃቶች በክልሉ የፀጥታ አካላት እየተፈፀሙ ነው ሲል ከሰሰ።

https://p.dw.com/p/3Xw3N
Äthiopien Arena Tigray, Opposition
ምስል DW/M. Hailessilassie

ዓረና ትግራይ ለሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው አለ

በትግራይ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዓረና ትግራይ ለሉኣላዊነትና ዴሞክራሲ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ እስር፣ አካላዊ ድብደባና ሌሎች ጥቃቶች በክልሉ የፀጥታ አካላት እየተፈፀሙ ነው ሲል ከሰሰ። በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ የሚፈፀሙ ጠቃቶች ዓረናን ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማገድ ያለሙ ናቸው ብሏል ፓርቲው። ፓርቲው ሰሞኑን የዓረና ስራ አስፈፃሚ አባል በሆኑ ዶክተር ማርቆስ ገሰሰ ላይ በመቐለ ጥቃት መፈፀሙ ገልፅዋል።

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ