1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የምሁራን አስተያየት

ረቡዕ፣ ሐምሌ 10 2011

ባሳለፍነው ሳምንት በመቐለ  በተካሄደ የምሁራን ውይይት ሕብረ ብሔራዊ የፌደራል ስርዓት ለኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ መሆኑ ተመለከተ። በውይይቱ ላይ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ ባቀረቡት ጽሑፍ በኢትዮጵያ ያለው ሕብረ ብሄራዊ ፌደራል ሥርዓት ለሀገሪቱ ህልውና ወሳኝ  እንደሆነ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3MCxm
[No title]

«የፌደራል ሥርዓት ለኢትዮጵያ ወሳኝ ነው»

ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ በትግራይ ከሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች የፖለቲካ አቀንቃኞች ጋር ባደረጉት ውይይት በቀጣይ ዓመት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቅ ምርጫ፣ ፌደራሊዝም እንዲሁም ሕገ መንግሥታት ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን አጋርተዋል። ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በውይይቱ ለመነሻነት ባቀረቡት ፅሑፍ በኢትዮጵያ ያለው ሕብረ ብሄራዊ ፌደራል ስርዓት ለሀገሪቱ ህልውና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ ከወታደራዊ መንግሥት በኋላ መተግበር የጀመረው ሕገ መንግሥት እና ፌደራላዊ ሥርዓት የሕዝቦች የዘመናት ጥያቄ የመለሰ መሆኑ የገለፁት ፕሮፌሰሩ ይሁንና ባለፉት ዓመታት በሚገባ ባለመተግበሩ ችግሮች መፈጠራቸው ጠቅሰዋል። ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል በሕገ መንግሥቱ መሠረት በመጪው ዓመት ይደረጋል ተብሎ ስለሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ «መንግሥትም ሆነ ሌላ አካላት ምርጫውን ማራዘም ወይ መቀየር አይችልም፤ አምስት ዓመት ካለፈ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ሕገ ወጥ ይሆናል» ብለዋል። በሌላ በኩል ምርጫው ለማካሄድ በቂ ዝግጅት መኖሩ የሚጠራጠሩ አካላት አሉ።  በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናቶች መምህር የሆኑት ቻላቸው ታረቀኝ «ምርጫውን የመካሄድ እና ጊዜውን የማራዘም ጉዳይ በመንግሥትና አስፈፃሚው አካል ዝግጁነት ይወሰናል» ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል የሕገ መንግሥቱን አነጋጋሪ አንቀፃች አስመልክተው ሲናገሩ o«አንቀፅ 39 የሕገ መንግሥቱ መልህቅ ነው» ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ