በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ከጄኔራል ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ-ምልልስ
ዓርብ፣ ጥር 6 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ባሁን ወቅት እየሠራ ያለው በሰሜን ኢትዮጵያ መንግሥትን የሚዋጋው የህወሓት ኃይል እስካልጠፋ የተረጋጋ ሰላም ሊመጣ እንደማይችል አቋም ይዞ መሆኑን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡ ጄኔራል ባጫ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ያሏቸው፤ ከውስጥ የሚልኳቸው ብኖራቸውም እንኳ ኢትዮጵያን ማሸነፍ እንደማይችሉ እስኪረጋገጥ የሚያበቃ ጦርነት የለም ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ በተወሰኑ አከባቢዎች ካሉ አነስተኛ ግጭት ውጪ ከባድ የሚባል ጦርነት የለም ያሉት ጄኔራሉ፤ በትግራይ ሲቪል ዜጎች ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት ይፈጸማል መባሉን አጣጥለው ነቅፈውታል፡፡
ስዩም ጌቱ
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ