1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በከማሺ ዞን የትምህርት ቤቶች ይዞታ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2011

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን  በመስከረም 2011ዓ.ም በዞኑ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ዘጠኝ  አንደኛ  ደረጃ ትምህርት ቤቶች እድሳት እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የዞኑ አተዳዳር አስታወቀ። 

https://p.dw.com/p/3OKmY
Äthiopien Schulen in der Benishangul-Gumuz Region
ምስል DW/N. Dessalegen

«ከ20 ሺህ በላይ ተማሪዎች ዘንድሮ አልተማሩም»

ሁለት ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመው እንደ ነበር የካማሺ ዞን አስተዳደር የሆኑት አቶ ታርኩ ኩመራ ለዶይቼ ቬለ DW ተናግረዋል። ከ20ሺ በላይ አንደኛ ደረጃ  ተማርዎች ደግሞ በትምህርት ገበታቸው ላይ አልነበሩም። ከመስከረም 2011 ዓ.ም መጀመሪያ  አንስቶ በካመሺ ዞን ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ከአምሳ ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል፣ በርካቶች ለሞት ተዳርጓል፣ በሚሊዩን የሚቆጠር ንብረት ደግሞ ባክኗል። ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ባንክ፣ ጤና ጣቢያዎችና ትምህርት ተቋማትም አገልግሎት መስጠት ከማቆም አልፎ የፈራረሱና የወደሙም  መኖራቸውን የካማሺ ዞን  ዋና አስተዳደር የሆኑት አቶ ታሪኩ ኩመራ ገልጸዋል። ለብዙ ወራት በነበረው አለመረጋጋት በካማሺ ዞንና በስሩ በሚገኙ   አጋሎሜጥ እና ቦሎ ጅጋንፎይ በተባሉ ወረዳዎች ዘጠኝ የሚደርሱ  አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና ከነዚህም ሁለት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶት ደግሞ ሙሉ በመሉ ወድመው  እንደ ነበር ነው የዞኑ አስተዳዳር አቶ ታሪኩ የገለጹት። የአሶሳው ዘጋቢያችን ነጋሳ ደሳለኝ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ