በኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ያገለገሉ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ቀረበ
ማክሰኞ፣ መስከረም 22 2011ማስታወቂያ
ጥሪ የተደረገላቸው በአማካኝ ከአራት እስከ 25 ዓመታት በአገልግሎት ዘርፍ ተቋሙን ያገለገሉት ባለሙያዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ «DW» ያነጋገራቸዉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም እንደገለፁት ጥሪ የተደረገላቸው ሠራተኞች በአገልግሎት ዘርፍ ከ 4 እስከ 25 ዓመታት የሠሩ ናቸው።
አቶ መለስ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ 58 ገደማ ሚሲዮኖች አሏት። አሁን ጥሪ የተደረገላቸው ሰራተኞች ከአንድ የተወሰነ ቦታ የተጠሩ እንዳልሆኑ አቶ መለስ ጨምረው ተናግረዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 130 ዲፕሎማቶች ስልጠና ተሰጥቷቸው በተለያዩ ኤምባሲዎች ለሥራ መመደባቸውን አስታውቋል። የተቋሙ አጠናሁት ያለው መዋቅር በጠቅላይ ምኒስትሩ ጸድቆ በቅርቡ የዲፕሎማቶች ዳግም ምደባ እንደሚደረግም አክሏል።
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ